፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 27 2016| NBC ETHIOPIA- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ የምርጫ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር ማሻሻያ አዋጅን አጸደቀ።
በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ የአዋጁን አስፈላጊነትና ተገቢነት አስመልክቶ እንደ ሀገር በተለያዩ ጊዜያት የተፈጠሩ የለውጥና የዲሞክራሲ ሽግግሮችን በአግባቡ ባለመጠቀማችን በግጭትና ጦርነት ውስጥ ቆይተናል። እስካሁን እንደ ሀገር እያገጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት በመንግስትና በህዝብ የተለያዩ ማሻሻያዎች እየተደረጉ ይገኛል።
ለዲሞክራሲ ግንባታ ማነቆ የሆኑ ህጎችን የማሻሻል ስራዎች እየተሰሩ ናቸው። የዚህ አዋጅ መጽደቀም መሰረታዊ ሀገራዊ ችግሮችን ለመሻገር ትልቅ ፋይዳ የሚኖረው ይሆናል ብለዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 30ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር የማሻሻያ አዋጅ በአብላጫ ድምፅ ማጽደቁን ኢ ፕ ድ ዘግቧል ።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












