፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 27 2016| NBC ETHIOPIA-የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያስተባባረ የሚገኘው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ዛሬ ለሰባተኛ ቀን እንደቀጠለ ነው።
የኅብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች፣ ሦስቱ የመንግሥት አካላት ተወካዮች፣ የማኅበራት እና ተቋማት ተወካዮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተወካዮች በአምስት ቡድኖች ተከፍለው ላለፉት ቀናት አጀንዳዎቻቸውን አስመዝግበዋል።
ከአምስቱ ባለድርሻ አካላት የተመረጡ ተወካዮች ደግሞ ዛሬ ግንቦት 27/2016 ዓ.ም በጠዋቱ ክፍለጊዜ የተሰበሰቡ አጀንዳዎችን እያደራጁ ነው።
ከሰዓት በኋላ በሚኖረው ክፍለጊዜ ደግሞ የተደራጁት አጀንዳዎች ለጉባኤው ይቀርቡና ምክክር ይደረግባቸዋል፡፡
በዚህ ምክክር የሚደራጁት አጀንዳዎች የአዲስ አበባ ከተማ የምክክር ምዕራፍ ውጤት ይሆናሉ፡፡
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












