፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 26 2016| NBC ETHIOPIA-በሱዳን እየተካሄደ የሚገኘው የእርስ በርስ ጦርነት በምግብ እና ሌሎች መሰረታዊ አቅርቦቶች ላይ መስተጓጎል መፍጠሩ ተገለጸ፡፡
በሱዳን ጦር ሰራዊትና በልዩ ሀይሉ መካከል መልሶ በተቀሰቀሰው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል፡፡

ልዩ ሀይሉ ተቆጣጥሮ በያዛቸው በሰሜን ካርቱም ባህሪ፤ ሀታብና ካድሮ ከተሞች ከባድ ውጊያ እየተደረገ መሆኑም ታውቋል፡፡
አንድ ዓመት የተሻገረው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ከሀገሪቱ አልፎ በቀጠናው በሚገኙ ሀገራት ላይ ፖለቲካዊ ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ጫና ማሳደሩን የዘገበው ቲ አር ቲ ወርልድ ነው ፡፡
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












