፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 26 2016| NBC ETHIOPIA-የሐሞት ጠጠር በሐሞት ከረጢት ውስጥ የሚፈጠሩ ትናንሽ ጠጠሮች ናቸው:: የሐሞት ከረጢት ጥቅም በሰውነታችን ውስጥ ቅባቶችን ለማዋሐድ የሚያግዝ ሐሞት የሚባል ፈሳሽ ማከማቸት እና ማመንጨት ነው፡፡

የሐሞት ጠጠር እንዴት ይፈጠራል?
ሐሞት በውስጡ ውሃ (97-98)% ፣ የሐሞት ጨው፣ ቢሊሩቢን እና ቅባቶችን (ኮሌስትሮል) ይይዛል። የሐሞት ፈሳሽ በጣም ብዙ ኮሌስትሮል ወይም ሌሎች ቆሻሻ ምርቶችን ከያዘ፣ እንዲሁም ሳይንቀሳቀስ ለብዙ ጊዜ ከቆየ ወደ ሐሞት ጠጠር ተቀይሮ ሊጠነክር ይችላል፡፡ ከዚያም ጠጠሩ ሐሞትን የሚያዘዋውሩ ቱቦዎችን በመዝጋት የሐሞት ፊኛ ሊያብጥ ይችላል፡፡
የሐሞት ጠጠር ምን ያህል ሰዎች ላይ ይከሠታል?

በአሜሪካ ውስጥ በግምት ወደ 6 ከመቶ ወንዶች እና 9 በመቶ ሴቶች ላይ ይታያል፡፡ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ የሐሞት ጠጠር በሽታ በተያዙ 747 ሕሙማን ላይ በተደረገ ጥናት መሠረት፤ ሴቶች ከወንዶች ይልቅ በ 5 እጥፍ የመያዝ ዕድላቸው ይጨምራል፡፡
ለሐሞት ጠጠር የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ምን ምንናቸው?

????በቤተሰብ ውስጥ የሐሞት ጠጠር ያለበት ሰው ከአለ፤
????ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ለዚህ በሽታ የተጋለጡ ናቸው፡፡
????ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣት፤
????ረዘም ያለ ጾም መጾም፤
????በፍጥነት ክብደት መቀነስ፤
????ዕድሜ መግፋት፤
????ከመጠን ያለፈ ውፍረት፤
????ነፍሰ ጡር መሆን፤
????የወሊድ መከላከያ ክኒን መጠቀም፤
????እንደ የስኳር በሽታ እና የጉበት በሽታ ያሉ በሽታዎች ሲኖሩ
የሐሞት ጠጠር ምልክቶች ምንድን ናቸው?

የሐሞት ጠጠር የአለባቸው አብዛኛዎቹ ሕመምተኞች ምንም ምልክቶች የላቸውም፡፡ ነገር ግን ምልክት ከአላቸው፤ የተለመደው ምልክት ከደረት ዝቅ ብሎ ጨጓራ አካባቢ ያለ ሕመም ስለሆነ፤ በብዛት በዚህ በሽታ የተጠቁ ሰዎች ለብዙ ዓመታት ለጨጓራ በሽታ ሲታከሙ የኖሩ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በቀኝ በኩል የላይኛው የሆድ ክፍል ላይ ሕመም ሊኖር ይችላል፡፡ ይህም ከ 30 ደቂቃ እስከ 6 ሰዓታት የሚቆይ የማያቋርጥ እና ከባድ የሚባል ሕመም ሲሆን ምግብ ከተመገቡ በኋላ ሕመሙ ይጨምራል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሕመሙ ወደ ጀርባ እና ትከሻ ሊሰራጭ ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የማቅለሽለሽ እና የማስታወክ ስሜት ሊኖር ይችላል፡፡
ሌሎች ምልክቶች እንደ ትኩሳት፣ የቆዳ እና የዐይን ቢጫ መሆን ከሐሞት ጠጠር ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን ሊያመለክቱ ይችላሉ፡፡ አልፎ አልፎ ሌሎች ያልተለመዱ ምልክቶችም ሊታዪ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፦
????የደረት ሕመም
????የሆድ መነፋት
????ቶሎ መጥገብ
????ቃር እና የመሳሰሉት ምልክቶች ተጠቃሾች ናቸው፡፡
????ከላይ የተገለጹት ምልክቶች ከታዩ ምን መደረግ አለበት?
የሐሞት ጠጠርን በሽታ እንዴት መከላከል ይቻላል?

????የሐሞት ጠጠር የመያዝ አደጋን ለመቀነስ
????መደበኛ የሰውነት ክብደትን መጠበቅ፤
????አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፤
????አልኮል መጠጥ እና ከፍተኛ ስብ ያላቸው ምግቦችን ማስወገድ፤
????እንዲሁም በየቀኑ ፋይበር እና ካልሲየም የያዙ ምግቦችን መመገብ፤
????ከመጠን በላይ ውፍረት ከአለ ክብደት መነስ፤ ሆኖም ግን በፍጥነት ክብደት ለመቀነስ መሞከር አይመከርም፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችን ማማከርና በጤናማ ሁኔታ ክብደት ለመቀነስ የሚያስችል ዕቅድ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡












