Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

በፈረንጆቹ ሰኔ ለእይታ ይበቃሉ ተብለው የሚጠበቁ ፊልሞች

June 3, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ግንቦት 26 2016| NBC ETHIOPIA-አለም አቀፍ ተቀባይነትን ባተረፉ ፊልም ጸሀፊያን  የሚጻፉ እና ታዋቂ ተዋንያኖች የሚሳተፉባቸው ፊልሞች ተቀባይነታቸው ከፍ ያለ እና በጉጉት የሚጠበቁ ናቸው ፡፡

ለፊልም አፍቃሪያን በመጪው የፈረንጆቹ ሰኔ ወር ለእይታ የበቃሉ ተብለው ከሚጠበቁ የባህር ማዶ ፊልሞች ልንነግራችሁ ወደድን፡፡

ባድ ቦይስ ራይድ ኦር ዳይ( Bad Boys Ride or Die)

የበርካቶች አድናቆት ተችሮታል እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር 1995 ታዋቂዎችን ተዋናዮች አጣምሮ  ለእይታ የበቃው… ባድ ቦይስ የተሰኘው የምርመራ የአክሽን ኮሜዲ ፊልም፡፡ የሆሊዉድ ፈርጦቹን ዊል ስሚዝ እና ማርቲን ላውረንስን አጣምሮ ከዚ ቀደም ለተመልካች በደረሱት  ባድ ቦይስ 1 ፣ ባድ ቦይስ 2 እንዲሁም በ 2020 በተለቀቀው ባድ ቦይስ ፎር ላይፍ  በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ተመልካቾችን ማግኘት ችሏል፡፡

 በመጪው ሰኔ ወር  ደግሞ ባድ ቦይስ ራይድ ኦር ዳይ የተሰኘ አራተኛ ከፍሉን ለተመልካቾን እንደሚያደርስ ይጠበቃል ፡፡  በታዋቂዎች  Adil El Arbi እና  Bilall Fallah ዳይሬክት የተደረገው ፊልሙ ቢቢሲ ባወጣው በሰኔ ወር ሊታዩ የሚገባቸው ምርጥ ፊልሞች ዝርዘር ውስጥ ተካቷል፡፡

ፊልሙም መርማሪዎቹ ማይክ ሎሬይ እና ማርከስ በርኔት በህይወት የሌሉት ካፒቴን ኮንራድ ሃዋርድ ከሮማኒያ ማፊያ ጋር ተሳትፈዋል ተብለው በተከሰሱበት ወቅት በማያሚ  ፖሊስ ዲፓርትመን ውስጥ  ያለውን ሙስና ለመመርመር ከህጉ ውጪ ለመሄድ ሲገደዱ እና ጉዳዩን ለማጣራት የሚያደርጉትን ጥረት በሳቅ እያዋዛ የሚያቀርብ ፊልም ነው ፡፡ ሰርቶ ለመጨረስም መቶ ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጎበታል፡፡  በመጪው የፈረንጆች ሰኔ ሰባት ለእይታ ይበቃል ተብሏል ፡፡

Inside Out 2

በአኒሜሽን ፊልም ጽሁፎቿ በምትታወቀው በሜግ ሌፋቭ እና ዴቭ ሆልስታይን ተጽፎ በ  Walt Disney Pictures ፕሮዲዩስ የተደረገው Inside Out ሁለት የተሰኘው  አኒሜሽን ፊልም በመጪው ሰኔ ወር ለእይታ ይበቃሉ ተብለው ከሚጠበቁ ፊልሞች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

የመጀመሪያው የፊልሙ ክፍል የሚያጠነጥነው አንድ ቤት በመቀየሩዋ የተበሳጨች   በአስራዎች የእድሜ ክልል ውስጥ የምትገኘው ታዳጊ ሀዘን ፣ ብስጭት ፣ ፍርሃት እና እንደ ቁጣ ያሉ ስሜቶች በአዕምሮዋ ውስጥ ሲጨቃጨቁ የሚያሳይ ነው፡፡ በሁለተኛው ክፍል ደግሞ አዳዲስ ስሜቶች በዋናነት ደግሞ የጭንቀት ስሜት ሲጨመር የሚያሳይ ፊልም ነው ፡፡ ፊልሙም በፈረንጆቹ ሰኔ 14 ለእይታ ይበቃል ተብሏል፡፡

Horizon: An American Saga – Chapter 1

ሌላኛው በሰኔ ወር ሊታዩ ከሚገባቸው ፊልሞች ዝርዝር ውስጥ የምናገኘው Horizon: An American Saga – Chapter 1 የተሰኘውን ፊልም ነው ፡፡ ፊልሙም ወደ ኋላ ተመልሶ ከአሜሪካ የእርስ በእርስ ጦርነት በፊት እና ከጦርነቱ በኃላ ያለውን የምዕራብ አሜሪካዊያንን መስፋፋት እና ሰፈራ የሚያሳይ ነው።

በታዋቂው አሜሪካዊ ተዋናይ፣ ጸሀፊ እና ፐሮዲዩሰር ኬቪን ኮስትረ ተጽፎ በራሱ ዳይሬክት ተደርጓል ፡፡ ዋናውን ገጸባህሪም ኬቪን ኮስትረ፣አቢ ሊ፣ሲና ሚለር እና ሌሎች ተሳትፈውበታል፡፡ Horizon: An American Saga – Chapter 1 ከሁለት ቀናት በፊት ለእይታ በቅቷል፡፡ ኬቪን ኮስትረ የፊልሙ ሌሎች ሶስት ተከታታይ ክፍሎች በቀጣይ ወራት ለእይታ እንደሚበቁ ተናግሯል፡፡

The Watchers

አንዲት የ28 አመት ወጣት በአየርላድ በሚገኝ አስፈሪ ጥቅጥቅ ያለ ደን ውስጥ መኪናዋ ይበላሽባት እና ትወርዳለች፡፡ በጫካ ውስጥም በምታገኘው ቤት ስትገባ ከማታውቃቸው ሶስት ሰዎች ጋር በማይታወቁ ፍጥሮች ከታሰረች በኃላ ለማምለጥ የሚያደርጉትን ሙከራ የሚያሳይ አስፈሪ ፊልም ነው The Watchers፡፡ ፊልሙ ከAM Shine መጽሃፍ መነሻውን አድርጎ  እንደተሰራ ተነግሯል ፡፡ ፊልሙ  የአንድ ሰአት ከ 42 ደቂቃ እርዝማኔ ሲኖረው ከሰኔ ሰባት ጀምሮ ለእይታ ይበቃል ተብሏል ፡፡

A Quiet Place: Day One

በሚካኤል ሳርኖስኪ ተጽፎ ዳይሬክት የተደረገው A Quiet Place: Day One ሌላኛው በሰኔ ወር ለእይታ ይበቃል ተብሎ በጉጉት እየተጠበቀ ያለ ፊልም ነው ፡፡ አስፈሪ ዘውግ ያለው ፊልሙ ከዚ ቀደም ሁለት ክፍሎች ሲኖሩት  በርካታ አለም አቀፍ ተመልካቾችንም ማትረፍ ችሏል፡፡  አዲሱ ክፍልም ከቀደመው ጋር ተመሳሳይ ሃሳብ ያለው ሲሆን አዲስ ገጸባህሪያትን አካቷል፡፡ ፊልሙ ከሌላ አለም  ተወርውረው  በኒዊውዮርክ ከተማ በሚወድቁ ኢሊየኖች ምክንያት ትርምስ ሲፈጠር ይጀምራል፡፡ ገጸ ባህሪያቱም ከእነዚህ ድምጽ ከማይፈልጉ ፍጥረቶች ለመደበቅ የሚያደርጉትን ጥረት የሚያሳይ ነው ፡፡ፊልሙም የሰው ልጆች ሊስማሙ ከማይችሉት ነገር ጋር እንዴት እንደሚስማሙ የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡ ሴኔ 27 ለእይታ ይበቃል፡፡

በ-የአብስራ ብርሀኑ

Tags: a quite place day onebad boys ride or dieinsideout2
ShareTweetShare
Previous Post

አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

Next Post

የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት

የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት

የፖለቲካ ፓርቲዎች ገዢውን ፓርቲ የሚገዳደሩበት ሳይሆን ለምክክሩ መሳካት የድርሻቸውን የሚያዋጡበት ሊሆን ይገባል ተባለ

የፖለቲካ ፓርቲዎች ገዢውን ፓርቲ የሚገዳደሩበት ሳይሆን ለምክክሩ መሳካት የድርሻቸውን የሚያዋጡበት ሊሆን ይገባል ተባለ

የምክር ቤቱ 3ዐኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ይካሄዳል

የምክር ቤቱ 3ዐኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ይካሄዳል

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?