፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 22 2016| NBC ETHIOPIA-በተለያዩ ወቅቶች የሚወጡ በርካታ የኪነ-ጥበብ ስራዎችን እና በዋናነት ተወዳጅነት ያተረፉ ፊልሞችን ደረጃ በመስጠት መረጃ የሚያጋራው Time Out የተሰኘው የለንደኑ ድህረገጽ በ2024 ተወዳጅነት እና እውቅናና ያገኙ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ ለዛሬ በምርጥነት ከተቀመጡ ተከታታይ ድራማዎቹ መካከል 5ቱን እናስቃኛቹ፡፡
1. Masters of the Air

መቼቱን በአሜሪካ ያደረገ ተከታታይ ድራማው የአክሽንና የሮማንስ የፊልም ዘውግ ያለው ሲሆን፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በምስራቃዊ እንግሊዝ ፣ በስምንተኛው አየር ኃይል ጦር በጦርነቱ የሚከፍለውን የህይወት ዋጋን ዙሪያ የሚያጠነጥን ተከታታይ ድራማ ነው፡፡ዘጠኝ ተከታታይ ክፍሎች ባሉት ተከታታይ ድራማ ኦስቲን በትለር፣ኮሉም ተርነር Callum Turner እና አንቶኒ ቦይል በዋና ገጸባህሪ ተጫውተዋል፡፡የካቲት 26 ለእይታ የቀረበው ድራማው አጠቃላይ 8፡31 ደቂቃ እርዝማኔ ያለው ሲሆን፣ በድህረገጹ ደረጃ በ5ተኛነት ተቀምጧል፡፡
2.ሪፕሊ

በአጠቃላይ 7፡30 ርዝማኔ ያለው ምናባዊ ገጸ ባህሪ ላይ ያተኮረ ተከታታይ ድራማ ነው፡፡በአሜሪካዊቷ ደራሲ ፓትሪሺያ ሃይስሚዝ የተደረሰው የወንጀል ልብ ወለድ ታሪክን መሰረት ተደርጎ ወደ ተከታታይ ድራማ የተቀየረው ተወዳጁ ሪፕሊ ከ2024 ምርጥ ተከታታይ ድራማዎች የ4ተኛውን ደረጃ ማግኘት ችሏል፡፡ አንድሪው ስኮት እና ዳኮታ ፋኒንግ የድራማው ዋና ገጸ ባህሪ በመሆን ተውነውበታል፡፡ ድራማውም 8ተከታታይ ክፍሎችን ያሉት ሲሆን ለእይታ ቀረበው ሚያዚያ 4 ነው፡፡ መቼቱን በጣሊያን ያደረገው ይህ ተከታታይ ድራማ፣ ዋነኛ ትኩረቱን ውስብስብ የወንጀል ታሪክ ላይ ማድረጉ ልብ አንጠልጣይነቱን አግዝፎለታል፡፡
3. ዋን ደይ

በአንድ ቀን ድንገታዊ ትውውቅ ኤማ እና ዴክ የተባሉ ዋና ገፀ-ባህሪውን የተላበሱት ተዋናዮች የህይወት አቅጣጫቸው ሲቀየር የሚያሳይ ድራማ ነው ዋን ደይ፡፡ ድራማው በአንድ ቀን ትውውቃቸው ለ2አስርት አመታት የዘለቀውን የፍቅር ታሪካቸውን እንዲሁም በአንድነት እና በተናጠል ያሳለፉትን አስቸጋሪ ወቅቶች የሚያስቃኝ ልብ አንጠልጣይ ተከታታይ ድራማ ነው፡፡
የካቲት 11 ለእይታ የቀረበው ድራማው 14 ተከታታይ ክፍሎች አሉት፡፡በሁለቱ ገፀ-ባህሪያት መካከል ለአመታት በዘለቀው ረዥም የፍቅር ታሪክ ውስጥ ያለፉ ውጣውረዶችን ፍንትው አድርጎ ያሳያል፡፡አምቢካ ሞድ እና ሊዮ ዉዳል ዋና ገጸ ባህሪውን በመወከል እና ሌሎች እውቅ ተዋንያዎች በድራማውን ተሳትፈዋል፡፡ ተከታታይ ድራማው ባገኘው ተወዳጅነት በሶስተኛ ደረጃ ተቀምጧል፡፡
4.Baby Reindeer

በሳሰለፍነው ወር ለእይታ የቀረበ እና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ተከታታይ ድራማ ነው፡፡ Baby Reindeer ….7 የትዕይንት ክፍሎችን የያዘው ድራማው ዶኒ ደን የተባለ ገጸ ባህሪ ኮሜዲያን ለመሆን የሚደርገውን ትግል እና በሚሰራበት ቦታ ከተዋወቃት ማርታ ከምትባል እንስት የሚገጥመው ከባድ ፈተና ላይ ያጠነጥናል፡፡ ማርታ የተሰኘችው ገጸ ባህሪ በዶኒ ደን በእያንዳንዱ የህይወት እንቅስቃሴው ውስጥ እንደ ጥላ በመከታተት በምታደርቻቸው ድርጊቶች ዶኒ የሚያሳልፈውን አወዛጋቢ ክስተቶችን በስፋት ያሳያል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የጠቀመጠው Baby Reindeer የ3፡57 ርዝማኔ ያለው ሲሆን በኔትፍሊክስ ለተመልካቾች ቀርቧል፡፡ ሪቻርድ ጋድ እና ጄሲካ ጉኒንግ በመሪ ገጸ በሃሪ ፊልሙን በድንቅ ብቃት ተውነውታል፡፡
5. ሾጉን

በጃፓን ከ1192-1867 በዘር የሚተላፍ የፊውዳል አገዛዝ ስርአት ነው ሾጉን፡፡ በ2024 ምርጥ ቁጥር አንድ ተከታታይ የቴሌቭዝን ድራማ ደረጃን ማግኘት ችሏል ሾጉን የተሰኘው የጃፓን ተከታታይ ድራማ፡፡ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው የሾጉን ድራማ ታሪኩ፤ ጄምስ ክላቬል በ1600 የጃፓን ስርወ መንግስት በንግስናው ወቅት ከአውሮፓ ሀገራት የሚደርስባቸውን ጫና በመታገል ያሳለፉትን ውጣ ውረድ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ከተዋንያን ሂሮዩኪ ሳናዳ፣ ታዳኖቡ አሳኖ፣ አና ሳዋይ እና ኮስሞ ጃርቪስ በርካታ ባለሙያዎች ተውነውበታል፡፡ የካቲት 27 ለእይታ የቀረበው ድራማው ታሪክን የኃሊት የሚያሳይ የአክሽን ዘውግ ያለው ድራማ ሲሆን 10 ክፍሎች አሉት፡፡












