Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

የዓለማችን ተወዳጁ ትኩስ መጠጥ-ሻይ

May 30, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ግንቦት 22 2016| NBC ETHIOPIA- በዕለት ተለት ህይወታችን ከማዕዳችን ፈጽሞ የማይለይ የማዕድ ድምቀት ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ ከሀብታም እስከ ዝቅተኛ ኑሮ ባላቸው ቤት  የማይጠፋ ከውሀ በመቀጠል በዓለም ዙርያ ሰዎች አብዝተው የሚጠቀሙት ትኩስ መጠጥ ነው። ሻይ

ለሰዎች ቅርብ ከመሆኑ የተነሳ በርካቶች የሆድ ሆዳቸውን ለመጨዋወት ‹‹ሻይ ቡና እንበል›› ሲሉም ይደመጣል፡፡

ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳለው የሚነገረው ሻይ ወደር የሌለው የዓለማችን ምርጡ መጠጥ ነው ሲሉ በርካቶችም ያሞካሹታል።

ታዲያ ይህ የብዙዎች ምርጫ የሆነው ሻይ ከየት ተገኘ ብለው ጠይቀው ከሆነ መልሱ ወደ ሩቅ ምስራቅ ያመራል።

አፈታሪክ እንደሚያስረዳው ሻይ ለመጀመሪያ ጊዜ መጠጣት የጀመረው ከ5 ሺህ አመት በፊት በቻይና ነበር። በ2737 የወቅቱ የቻይና ንጉሠ ነገሥት ሼን ኑንግ በሻይ ቅጠል ዛፍ ስር ውሃ ሲያፈሉ ቅጠሉ ወደ ማፍያው ገብቶ የውሃውን ቀለም እና መዓዛን ስለመለወጡ ይነገራል። ቀለሙ እና ጣዕሙ  በቻይናው ንጉሰ ነገስት  የተወደደው  ቅጠል  አሁን ላይ ሻይ ብለን እንጥራው እንጂ በወቅቱ የነበረው  የዛፍ ስም ካሜሊያ ሲነንሲስ ይሰኝ ነበር።  

ፖርቹጋል እና ደች በ1610 ለመጀመሪያ ጊዜ ሻይን ወደ አውሮፓ ያመጡ ሀገራት  ናቸው ። በእንግሊዝ ውስጥ ሻይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቀው ደግሞ በንጉስ ቻርለስ ሁለተኛ ሰርግ ላይ መሆኑ ይነገራል፡፡

በንጉሠ ነገሥቱ  ሼን  ዮንግ የተወደደው ሻይ እያለ መላው ቻይናን ብሎም ፣ በጃፓን በአሜሪካ እንዲሁም በመላው ዓለም ተዳረሰ፡፡

እስከ 17ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ ሁሉም ቻይናውያን ይጠቀሙት የነበረው የሻይ ዝርያ አረንጓዴ ሻይ እንደነበር ይነገራል፡፡ የሻይ ተፈላጊነት እየሰፋ እና የውጭ ንግድ እየጨመረ በሄደ ቁጥር የሻይ ቅጠል ዝርያዎች እየተበራከቱ እና ጣዕምና ምርታቸው እየታከለበት ሄደ፡፡

ሻይ በዓለም ላይ ከውሃ ቀጥሎ ሰዎች በብዛት የሚጠቀሙት ሁለተኛው መጠጥ  ሲሆን፣ አሁን ላይ ከ1,500 በላይ የተለያዩ  የሻይ ቅጠል ዝርያዎች ይገኛሉ ። የሻይ ተክሎች በእስያ ክፍሎች ባሉ በደኖች በስፋት ይበቅላሉ። ከ 25 በላይ አገሮች ደግሞ ሻይን እንደ ተክል በማምረት ኢኮኖሚያቸውን ይደግፉበታል፡፡

ዘርፈ በዙ ጥቅሞች እንዳሉት የሚነገርለት ሻይ ትኩረትን ለመሰብሰብ ፣ዘና ለማለት ፣ ስኳርን ለመቆጣጠር እንዲሁም በርካታ የጤና ጥቅሞች አሉት፡፡

የሻይ ተክል በአሁኑ ጊዜ በአራት ትልልቅ ሻይ አምራች አገሮች በሆኑት፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ስሪላንካ እና ኬንያ በብዛት ይመረታል። ሀገራቱ የዓለምን 75 በመቶ የሻይ ምርት ይሸፍናሉ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀን ሦስት ቢሊዮን ኩባያ ሻይ እንደሚጠጣ  ይገመታል። አሁን ላይ በዓመት የሚመረተው የሻይ መጠን ከ6 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ቶን የደረሰ ሲሆን፣ የተጠቃሚዎች ቁጥር በዓመት ከ3 በመቶ በላይ እያደገ ስለመሆኑም ይነገራል።

በአለም ላይ ሻይ በመጠጣት ቀዳሚዎቹ ቱርካውያን ናቸው። ከ10 ቱርካውያን ዘጠኙ ሻይ እንደሚጠቀሙ ጥናቶች ያመልካታሉ።

እንደ አለም የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) መረጃ በ2022 6 ነጥብ 7 ሚሊየን ቶን ሻይ ተመርቷል፡፡

በሻይ ተክል ምርት ላይ የሚንቀሳቀሰው ገንዘብም አሁን ላይ የትየለሌ ደርሷል፡፡ እ.ኤ.አ በ2025 134 ቢሊየን ዶላር የሻይ ተክል ምርት ላይ ፈሰስ የሚደረግ ገንዘብ ይሆናል ተብሎ ተገምቷል፡፡  

በዓለም ላይ ካሉት በጣም  ውድ የሻይ ዝርያዎች  የቻይናው ዳ ሆንግ ፓኦ ቁጥር አንዱ ሲሆን፣ እንደየጥራት ደረጃው የዳ ሆንግ ፓኦ ሻይ ቅጠል በኪሎ ከሺዎች እስከ አስርሺዎች ዶላር ይሸጣል።

በ- ሀይማኖት ወርቁ

ShareTweetShare
Previous Post

የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት በሩስያ

Next Post

32ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ተካሄደ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
32ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ተካሄደ

32ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ተካሄደ

በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኝው የምክክር ምዕራፍ የአጀንዳ ማሰባሰብ መርሀግብር

በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኝው የምክክር ምዕራፍ የአጀንዳ ማሰባሰብ መርሀግብር

የዓለማችን ትንሿ ሀገር-ቱቫሉ

የዓለማችን ትንሿ ሀገር-ቱቫሉ

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?