፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 22 2016| NBC ETHIOPIA-የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ29ኛ መደበኛ ስብሰባው የማዕድን ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እየገመገመ ነው፡፡
-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጎነት ተብሎ በተሰየመው የመኖሪያ መንደር የተገነቡ ሁለት ባለ 9 ወለል ዘመናዊ ሕንጻዎችን እና የስራ ዕድል መፍጠሪያ ማዕከላትን በመመረቅ ለ140 አቅመ ደካሞች እና አካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች አስተላልፈዋል።
-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ “ቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ 2024″ አውደ ርዕይን በይፋ አስጀመሩ፡፡
-የምክክር ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን በባለቤትነት ስሜት እየሰራን ነው ሲሉ በአዲስ አበባ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ተሳታፊ አካል ጉዳተኞች ገለጹ።
-የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የወጭና ገቢ ንግድን በማጠናከር ለሀገሪቷ የምጣኔ ሃብት እድገት የላቀ ሚና መወጣት አለበት ተባለ፡፡
-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በመዲናዋ 218 ቦታዎች ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ናቸው አለ፡፡
-በኢትዮጵያ የእናቶችና የህጻናት ጤናን በማሻሻል ሞትን መቀነስ መቻሉን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።
-10ኛው ዙር ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው ።
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












