Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ዘመን አይሽሬ የዓለማችን ምርጥ ልቦለዶች

May 29, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ግንቦት 21 2016| NBC ETHIOPIA- ልቦለድ ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እሴቶች እንዲሁም ምዕናባዊ ፈጣራዎች በጣፈጠ የአጻጻፍ ለዛ ተሰፍተው ለአንባቢያን የሚቀርብበት የገሀዱ ዓለም ነጸብራቅ የሆነ የኪነጥበብ ዘርፍ ነው።

በየዘመናቱ ለአንባቢያን የሚደርሱ በርካታ የልብ ወለድ ስራዎች ከዘመን ዘመን በመሸጋገር አይረሴ ሆኖው መዝለቅ ችለዋል። የግዜ መርዘም ካላደበዘዛቸው እና ትልቅ ማህበራዊ ተፅእኖን ማሳደር ከቻሉ እንዲሁም የበርካቶች ቀልብን መግዛት ከቻሉ ከዓለማች ምርጥ ልቦለዶች መካከል የተወሰኑትን መርጠን እናስቃኛችሁ።

1, አና ካሬኒና (Anna Karenina)

ዘመን የማይሽረው ከትውልድ ትውልድ ሲሸጋገር የዘለቀ ድንቅ ስራ ነው ሲሉ ብዙዎች ይመሰክሩለታል። በሩሲያው ደራሲ ሊዮ ቶልስቶይ የተጻፈ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ ከ1875 እስከ 1877 በተለያየ ክፍሎች የታተመ እና ከዓለም የሥነ-ጽሑፍ ስራዎች መካከል ቁንጮ መሆን የቻለ ነው፡፡

አና ካሬኒ የተሰኘው ልብወለድ ዛሬም ድረስ በብዙ አንባቢያን ዘንድ ከአእምሮ ከማይጠፋ ድንቅ ልቦለዶች አንዱ ነው፡፡ ልቦለዱ በስምንት ምዕራፎች የተሰደረ ሲሆን፣ የሁለት ዋና ገጸ-ባህሪያትን ታሪክ ይተርካል። ታሪኩም አና የተባለች ኮረዳ አሌክሲ ኪሪሎቪች ከተባለ  አንድ ባለጸጋ ወጣት ጋር ከጋብቻ በፊት በፈጠሩት ግንኙነት የደርስባቸውን ማህበራዊ ውጣውረድ ፍንትው አድርጎ ያሳያል።

አና ካሬኒና ልቦለድ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በሩሲያ ውስጥ የነበረን ፍቅርን, ታማኝነትን እና የህብረተሰብን ግንኙነትን  ይዳስሳል።

በልብ ወለዱ ከትዳር ውጪ የሚደረጉ የፍቅር ግንኙነቶች የሚያስከፍሉትን ዋጋ  ፣ ከማህበረሰብ እሴት ያፈነገጡ ተግባራት የሚያስከፍሉት ዋጋ በጉልህ ተነስተውበታል፡፡

በሌላ በኩል መጽሀፉ በሩሲያ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የነበረውን የባላባት ቤተሰቦች ወግ አጥባቂ ማህበራዊ አኗኗሮችን ይተቻል።

ልቦለዱ በዓለም ላይ ታዋቂነት እና  ዝናን እንዲያገኝ፣  የልቦለዱ ግጭት፣ መቼት፣ እንዲሁም ጥልቀት የደራሲው የታሪክ ፍሰት አሰዳደር እና ሌሎች የልቦለድ አላባውያን ጥራት በዓለም የስነ-ጽሑፍ ታሪክ ትልቅ ስኬት እንዲገኝ አስተዋፅዖ አድርገዋል።

የአና ካሬኒና ልዩ ገጸ-ባህሪያት እና ትረካ  ሙሉ በሙሉ የደራሲው የምናባዊ  ፈጠራዎች ናቸው። ቶልስቶይ ስለ ሩሲያ ማህበረሰብ ያለውን ጥልቅ ግንዛቤ፣ ስለራሱ ግላዊ ገጠመኞች እና ስለ ሰው ተፈጥሮ ያለውን ጥልቅ ምልከታ ተጠቅሞ ይህን አስደናቂ ልቦለድ ለአንባቢያን አበርክቷል፡፡ ልቦለዱ ከዓመት ዓመት በተወዳጅነት የዘለቀ  ድንቅ ሥራ መሆን ችሏል።

ልቦለዱ ከምን ጊዜም ከፍተኛ ሽያጭ ካላቸው መጽሃፎች አንዱ ሰለመሆኑም መረጃዎች ያመላክታሉ። ልቦለዱን መሰረት አደርገውም በርካታ ፊልሞች ተሰርተዋል።

2, ቱ ኪል ሞኪንግበርድ (To Kill a Mockingbird)

ሞኪንግበርድን ልቦለድ እ.ኤ.አ በ1960 በአሜሪካዊቷ ደራሲ ሃርፐር ሊ የተደረሰ  ተወዳጅ የዓለማችን ልቦለድ ነው። ሞኪንግበርድን ልቦለድ እትሙ ለአንባቢያን ከደረሰ ከአንድ አመት በኋላ የፑሊትዘር ሽልማትን ማሸነፍ ችሏል።

ልቦለዱም ጊዜ የማይሽረው የሥነ-ምግባር፣ የፍትህ እና የሰውን ሁኔታ ከሚዳስሱ የዓለማችን ታላላቅ  ልብ ወለዶች ተረታ የተቀመጠ ነው።

በዓለም ዙሪያ ከ40 ሚሊዮን በላይ ቅጂዎችን በመሸጥ ከምን ጊዜም ከፍተኛ ሽያጭ ካላቸው ልብ ወለዶች ተርታ መሰለፍ ችሏል፡፡

ልቦለዱ በጊዜው የነበሩትን ታዋቂ ማህበራዊ ጉዳዮችን ማለትም የዘር እኩልነትን እና የሞራል ትምህርትን ይዳስሳል።

ልቦለዱ በደቡብ አሜሪካ በወቅቱ ስለነበረው ታላቅ የኢኮኖሚ ውድቀት እና የቀለም ልዩነትን ተከትሎ የሚደረጉ መገለል እና አድሎዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ቢሆንም፣ የታሪኩ ገፀ-ባህሪያት፣ ሁነቶች እና ሴራዎች ሙሉ በሙሉ የምዕናብ ታሪኮች ናቸው።

ልቦለዱም እ.ኤ.አ. በ1930ዎቹ በነበረው የኢኮኖሚ ድቀት ወቅት በሜይኮምብ ፣ አላባማ ከተማ ስላደገች ወጣት ልጅ ታሪክ ያስነብባል። የወጣቷ አባትም በከተማዋ ስር የሰደደ የዘር ጭፍን ጥላቻ ቢኖርም በወንጀል የተከሰውን ጥቁር ሰው ለመከላከል በጀግንነት ለፍትህ እና  ለነጻነት የሚደረግ ትግልን ይተርካል፡፡

መጸሀፉም የዘር መድልዎ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ በሚያስደንቅ ሁኔታ በግልጽ የሚያሳይ ነው።ልቦለዱን መሰረት የተሰራ ፊልም ተወዳጅነት ማትረፍ ችሏል፡፡

የደራሲዋ የተዋጣለት አተራረክ፣ የልቦለዱ የጭብጥ ጥልቀት፣ በታሪክ የተመሰረተ ግን ዘመን የማይሽራቸው ግንዛቤዎች እና የማይረሱ ገፀ ባህሪያቶቹ ጥምረት ልቦለዱ እስከ ዛሬ ድረስ ተጽኖ ፈጠሪ እና ተወዳጅ ሆኖ እንዲቀጥል አስተዋጾ አድርጓል።

3, ዘ ግሬት ጋትቢ ( The Great Gatsby)

The Great Gatsby እ.ኤ.አ.በ1925 በአሜሪካዊው ጸሃፊ ኤፍ.ስኮት ፊዝጀራልድ የተደረሰ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን ታላላቅ ስራዎች መካከል አንዱ እና ዘመን አይሽሬ ድንቅ መጸሀፍ ነው።

ታሪኩ በ1920ዎቹ በኒውዮርክ ሲቲ መቼቱን አድርጓል።ሚስጥራዊው ሚሊየነር ጄይ ጋትስቢን እና የቆንጆዋን ዴዚ ቡቻናንን የፍቅር ታሪክ ይዳስሣል። ይህ  ልብ ወለድ በበርካታ በአንባቢ ትውልዶች ዘንድ  አድናቆትን አግኝቷል።

የፊዝጄራልድ ልዩ ጽሑፍ፣ የልቦለዱ የጭብጥ ጥልቀት፣ እና ዘላቂ የባህል ተፅዕኖው ጥምረት ልቦለዱን እውነተኛ የአሜሪካ የሥነ-ጽሑፍ ክላሲክ አድርጎታል።

እ.ኤ.አ በ1925 ለአንባቢያን የደረሰው ልቦለዱ የወቅቱን የነበሩትን ማህበራዊ ጉዳዮች ፣ የፍቅር ህይወትን ፣ ዓመፅን እንዲሁም የጨቋኝ ባለሀብቶች ድርጊት እና ያስከተለባቸውን አሉታዊ መዘዝ ያስነብባል።

The Great Gatsby ልቦለድ በዓለም ዙሪያ ከ 25 ሚሊዮን በላይ ቅጂዎች ተሽጠውለታል። ልቦለዱን መሰረት አደርገውም በርካታ ፊልሞች ተሰርተዋል።

ShareTweetShare
Previous Post

የአዲስ አበባ የምክክር ምዕራፍ ማስጀመሪያ መርሃግብር

Next Post

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በወቅታዊ የክልሉ ጉዳዮች ማብራሪያ ሰጡ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
50
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በወቅታዊ የክልሉ ጉዳዮች ማብራሪያ ሰጡ

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በወቅታዊ የክልሉ ጉዳዮች ማብራሪያ ሰጡ

የ2024 የዓለም ምርጥ መዳረሻዎች

የ2024 የዓለም ምርጥ መዳረሻዎች

የህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ 40 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ።

የህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ 40 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ።

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?