Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Health

ትኩረት የተነፈጋቸው ተላላፊ በሽታዎች

May 27, 2024
in Health, News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ግንቦት 19 2016| NBC ETHIOPIA- ከቅርብ አመታት  ወዲህ ትኩረት እያጡ የመጡ እንደ ኤች አይቪ ኤድስን እና ሌሎች  ተላላፊ በሽታዎች ስርጭት  በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ መሆኑን የአለም ጤና ድርጅት ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል፡፡  

ኤች ኤይቪ ፣ ሄፓታይተስ ቫይረስ እና ሌሎች በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች በአለም አቅፍ ደረጃ በህብረተሰብ ጤና ላይ እክል እየፈጠሩ እንደሆነ WHO አስታውቋል፡፡

በእነዚህም በሽታዎች  ሳቢያ በአመት ከሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን እያጡ እንደሆነም ነው በሪፖርቱ የተገለፀው፡፡

ይህ የጤና እክል ከፍተኛ ስርጭት አለባቸው ተብሎ በሚታሰቡ ሀገራት በ2030 የበሽታውን ስርጭት ከ 7.8 ወደ 0.7 በአስር እጥፍ ለመቀነስ የአለም ጤና ድርጅት እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጿል፡፡

ባሳለፍነው ፈረንጆቹ አመት SYPHILIS ተብሎ የሚጠራው በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፈው  ቫይረስ  ከ15 እስከ 49 የእድሜ ክልል የሚገኙ አንድ ሚሊዮን ሰዎችን ማጥቃቱ ተገልጿል፡፡ በዚም አጠቃላይ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ወደ ስምንት ሚሊዮን ከፍ ሊል ችሏል፡፡ ስርጭቱም በአሜሪካ እና በአፍሪካ በሚገኙ ሀገርት ላይ ልቋል ይላል የተቋሙ መረጃ፡፡

እየጨመረ የመጣው በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች  ትልቅ ስጋት እየፈጠሩ ነው ያሉት  የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም በሌላ በኩል ወሳኝ የሆኑ የህክምና ግብአቶችን ተደራሽነት ከመጨመር አኳያ በዘርፉ ላይ መሻሻሎች መታየታቸውን ተናግረዋል።

ድርጅቱ በ2030 ለማህበረሰብ ጤና ጠንቅ የሆኑ ወረርሽኞችን ለመከላከል የሚያስፈልጉ  መሳሪያዎች ሁሉ እንዳለው የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ስርጭቱን በመከላከል ሂደት  አገራት  የራሳቸው ስትራቴጂ  ለማሳካት የተቻላቸውን ሁሉ ሊያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ባለፉት አመታት በኤች ኤይቪ ኤድስ ላይ የተደረገው ዘመቻ የሚታይ ለውጥ የተመዘገበበት ቢሆንም አሁን ላይ ከግብረስጋ ግንኙነት ጋር ተያያዞ የሚከሰቱ በሽታዎች ቁጥር መጨመር ቫይረሱ ዳግም እንዳያንሰራራ አድርጎታል ነው የተባለው፡፡

ከግብረስጋ ግንኙነት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ሊታከሙ የሚችሉ በሽታዎች አሁን ላይ በቀን አንድ ሚሊዮን አዳዲስ ኬዞች እየተመዘገቡ እንደሆነም ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

በ2022 ወደ 1.2 ሚሊዮን የሚጠጉ አዳዲስ የሄፐታይተስ ቢ ተጠቂዎች እና አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ  የሄፐታይተስ ሲ ተጠቂዎች ተመዝግበዋል፡፡

ምንም እንኳን ውጤታማ የመከላከያ፣ የምርመራ እና የህክምና መሳሪያዎች ቢኖሩም  በሄፓታይተ ስ ቫይረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር እ.ኤ.አ. በ2019 ከነበረበት 1.1 ሚሊዮን በ2022 ወደ 1.3 ሚሊዮን ከፍ ብሏል፣

ኤችአይቪ ኤድስን በተመለከተ በ2020 ከነበረበት 1.5 ሚልዮን ወደ 1.3 ቅናሽ ያሳየ ቢሆንም አሁንም ከጠቅላላው ህዝብ ጋር ሲነፃፀር በተወሰኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ውስጥ ኤች.አይ.ቪ በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራጨ ነው ተብሏል፡፡

በዚህ ወቅት  በኤችአይቪ ኤድስ  የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ማሻቀቡ የተሰማ ሲሆን፡፡

እንደሪፖርቱ ገለጻ በ2022 630 ሺህ ሰዎች ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን ሲያጡ 13 በመቶ የሚሆኑት እድሜያቸው ከ15 አመት በታች የሚገኙ ህጻናት ናቸው፡፡

የኤችአይቪ ኤድስ ህክምና እና ክትትል ባለፉት አመታት በ73 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱም ተመላክቷል፡፡ የበሽታዎችን መስፋፋት ተከትሎ ሀገራት በበሽታው ዙርያ ዘላቂ እቅዶች እና ፖሊሲዎችን ነድፈው  በትኩረት መስራት እንዳለባቸው የአለም ጤና ድርጅት አሳስቧል፡፡ በተለይ በወጣቶች እና ታዳጊዎች አካባቢ ያለው ስርጭት አሳሳቢ በመሆኑ ወላጆች የልጆቻቸውን  ሁኔታ እንዲከታተሉ ምክረ ሀሳቡን አስቀምጦል፡፡

በ-የአብስራ ብርሀኑ

ShareTweetShare
Previous Post

የአየር ንብረት ለውጥ በትምህርት ዘርፉ ያሳደረው ጫና

Next Post

ሃገራዊ ምክክሩ የምክክር ምዕራፉን ግንቦት 21 በአዲስ አበባ ይጀምራል-ኮሚሽኑ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
51
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ሃገራዊ ምክክሩ የምክክር ምዕራፉን ግንቦት 21 በአዲስ አበባ ይጀምራል-ኮሚሽኑ

ሃገራዊ ምክክሩ የምክክር ምዕራፉን ግንቦት 21 በአዲስ አበባ ይጀምራል-ኮሚሽኑ

በኮርያ ልሳነ ምድር እየተካረረ የመጣው ውጥረት

በኮርያ ልሳነ ምድር እየተካረረ የመጣው ውጥረት

አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?