፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 19 2016| NBC ETHIOPIA- ከቅርብ አመታት ወዲህ ትኩረት እያጡ የመጡ እንደ ኤች አይቪ ኤድስን እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ መሆኑን የአለም ጤና ድርጅት ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል፡፡
ኤች ኤይቪ ፣ ሄፓታይተስ ቫይረስ እና ሌሎች በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች በአለም አቅፍ ደረጃ በህብረተሰብ ጤና ላይ እክል እየፈጠሩ እንደሆነ WHO አስታውቋል፡፡
በእነዚህም በሽታዎች ሳቢያ በአመት ከሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን እያጡ እንደሆነም ነው በሪፖርቱ የተገለፀው፡፡
ይህ የጤና እክል ከፍተኛ ስርጭት አለባቸው ተብሎ በሚታሰቡ ሀገራት በ2030 የበሽታውን ስርጭት ከ 7.8 ወደ 0.7 በአስር እጥፍ ለመቀነስ የአለም ጤና ድርጅት እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጿል፡፡
ባሳለፍነው ፈረንጆቹ አመት SYPHILIS ተብሎ የሚጠራው በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፈው ቫይረስ ከ15 እስከ 49 የእድሜ ክልል የሚገኙ አንድ ሚሊዮን ሰዎችን ማጥቃቱ ተገልጿል፡፡ በዚም አጠቃላይ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ወደ ስምንት ሚሊዮን ከፍ ሊል ችሏል፡፡ ስርጭቱም በአሜሪካ እና በአፍሪካ በሚገኙ ሀገርት ላይ ልቋል ይላል የተቋሙ መረጃ፡፡

እየጨመረ የመጣው በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች ትልቅ ስጋት እየፈጠሩ ነው ያሉት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም በሌላ በኩል ወሳኝ የሆኑ የህክምና ግብአቶችን ተደራሽነት ከመጨመር አኳያ በዘርፉ ላይ መሻሻሎች መታየታቸውን ተናግረዋል።
ድርጅቱ በ2030 ለማህበረሰብ ጤና ጠንቅ የሆኑ ወረርሽኞችን ለመከላከል የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች ሁሉ እንዳለው የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ስርጭቱን በመከላከል ሂደት አገራት የራሳቸው ስትራቴጂ ለማሳካት የተቻላቸውን ሁሉ ሊያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ባለፉት አመታት በኤች ኤይቪ ኤድስ ላይ የተደረገው ዘመቻ የሚታይ ለውጥ የተመዘገበበት ቢሆንም አሁን ላይ ከግብረስጋ ግንኙነት ጋር ተያያዞ የሚከሰቱ በሽታዎች ቁጥር መጨመር ቫይረሱ ዳግም እንዳያንሰራራ አድርጎታል ነው የተባለው፡፡
ከግብረስጋ ግንኙነት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ሊታከሙ የሚችሉ በሽታዎች አሁን ላይ በቀን አንድ ሚሊዮን አዳዲስ ኬዞች እየተመዘገቡ እንደሆነም ሪፖርቱ ያሳያል፡፡
በ2022 ወደ 1.2 ሚሊዮን የሚጠጉ አዳዲስ የሄፐታይተስ ቢ ተጠቂዎች እና አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ የሄፐታይተስ ሲ ተጠቂዎች ተመዝግበዋል፡፡
ምንም እንኳን ውጤታማ የመከላከያ፣ የምርመራ እና የህክምና መሳሪያዎች ቢኖሩም በሄፓታይተ ስ ቫይረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር እ.ኤ.አ. በ2019 ከነበረበት 1.1 ሚሊዮን በ2022 ወደ 1.3 ሚሊዮን ከፍ ብሏል፣
ኤችአይቪ ኤድስን በተመለከተ በ2020 ከነበረበት 1.5 ሚልዮን ወደ 1.3 ቅናሽ ያሳየ ቢሆንም አሁንም ከጠቅላላው ህዝብ ጋር ሲነፃፀር በተወሰኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ውስጥ ኤች.አይ.ቪ በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራጨ ነው ተብሏል፡፡
በዚህ ወቅት በኤችአይቪ ኤድስ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ማሻቀቡ የተሰማ ሲሆን፡፡
እንደሪፖርቱ ገለጻ በ2022 630 ሺህ ሰዎች ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን ሲያጡ 13 በመቶ የሚሆኑት እድሜያቸው ከ15 አመት በታች የሚገኙ ህጻናት ናቸው፡፡
የኤችአይቪ ኤድስ ህክምና እና ክትትል ባለፉት አመታት በ73 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱም ተመላክቷል፡፡ የበሽታዎችን መስፋፋት ተከትሎ ሀገራት በበሽታው ዙርያ ዘላቂ እቅዶች እና ፖሊሲዎችን ነድፈው በትኩረት መስራት እንዳለባቸው የአለም ጤና ድርጅት አሳስቧል፡፡ በተለይ በወጣቶች እና ታዳጊዎች አካባቢ ያለው ስርጭት አሳሳቢ በመሆኑ ወላጆች የልጆቻቸውን ሁኔታ እንዲከታተሉ ምክረ ሀሳቡን አስቀምጦል፡፡
በ-የአብስራ ብርሀኑ












