፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 09 2016| NBC ETHIOPIA- በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ በማራቶን ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ይፋ ሆኑ በወንዶች ማርቶን ሲሳይ ለማ፣ ዱሬሳ ገለታና ቀነኒሳ በቀለ ሲመረጡ፣ ታምራት ቶላና ኡሰዲን መሐመድ በተጠባባቂነት ተይዘዋል፡፡
-በሴቶች ማርቶን ትዕግስት አሰፋ፣ አማኔ በሪሶና መገርቱ አለሙ ሲመረጡ፤ጎይተቶም ገ/ስላሴና ቡዜ ድሪባ በተጠባባቂነት የተመረጡ አትሌቶች ናቸው፡፡
-በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወላይታ ድቻን 5 ለ 0 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
-የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ካርሎ አንችሉቲ የአማካኝ ተጫዋቹ ጁድ ቤሊንግሃም በቀጣይ የውድድር ዓመት ወደ ጥልቅ የጨዋታ ሚና እንዲመለስ ማቀዳቸው ተነግሯል፡፡
-የማንችስተር ሲቲ ግብ ጠባቂ ኤደርሰን ሞራይስ በጉዳት ሳቢያ ከቀሪ ጨዋታዎች ውጪ ሆኗል፡፡
-ስፔናዊው የመስመር ተጨዋች ሄሱስ ናቫስ በውድድር አመቱ መጨረሻ ከሲቪያ ጋር ይለያያል ተብሏል፡፡
-ፊሊፔ ኩቲኒሆወደ ብራዚል ሊግ ተመልሶ ሊጫወት እንደሚችል ተገልጿል፡፡
– ተጠባቂው የከባድ ሚዛን ቡጢ ሻምፒዮና የፊታችን ቅዳሜ በሳዑዲ አረቢያ በታይሰን ፊዩሪና ኦሌክሳንደር ኡሲክ መካከል ያካሄዳል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












