፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 21 2016| NBC ETHIOPIA-የ2016 የትምህርት ዘመን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ 12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት፡-
– ለማህበራዊ ሳይንስ ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም
-ለተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 9-11/ 2016 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን ፈተናው በበይነ መረብ (ኦን ላይን) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።
በወረቀት የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30 እና ሐምሌ 01/2016 ዓ.ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6 እና 7/2016 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ እና ተፈታኞችና የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












