፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 16 2016| NBC ETHIOPIA- የአለም ሀገራት የከተሞቻቸውን ደረጃ ለማስጠበቅ በመሰረተ ልማት ግንባታ፣ውበትን በማስጠበቅ እና የተበከለ አየርን ለመቀነስ ቀን ከሌት ያለ እረፍት እየሰሩ ይገኛሉ።
አለም አቀፉ ግሎባል ዴስቲኔሽን ሰስቴነብሊቲ ኢንዴክስ ሀገራት ያላቸውን የአየር ብክለት ደረጃ፣ የከተማ ንጽህና፣ ምቹ መንገዶች፣ የሆቴል ክፍሎች ንጽህና፣ተረፈ ምርቶችን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል እና በሌሎች 69 መስፈርቶች በመለየት ከተሞችን ገምግሜያለው ብሏል።
በዚህም የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ እየሰሩ ያሉ እና ለቱሪስቶችም ሆነ ለነዋሪወች ምቹ በመሆን አለምን የተሻለ ስፍራ ሊያደርጓት ይችላሉ ያላቸውን ከተሞች ይፋ አድርጎል።
እንደ ግሎባል ዴስቲኔሽን ሰስቴነብሊቲ ኢንዴክስ መረጃ ዘላቂ የቱሪስት መዳረሻ ደርጃን እ.አ.አ ከ 2016 እስከ 2021 ድረስ አንደኛ በመሆ የዘለቀችው የስዊድን ሁለተኛዋ ትልቋ ከተማ ጎተንበርግ ናት።

በከተማዋ 97 በመቶ ተሽከርካሪዎች በታዳሽ ሀይል የሚሰሩ መሆናችው ከተማዋ የንጹ አየር ባለቤት እንድትሆን አስችሏታል።
አየር መንገዶቿም ቢሆን የካርበን ልቀትን ለመቆጣጠር ባላቸው ቁርጠኝነት እውቅና ተችሮቸዋል። በአለም ላይ አረንጓዴ እና ሙሉ በሙለ ማለት በሚያስበል ደረጃ የአካባቢ ጥበቃን ማረጋገጥ ቻሉ ሆቴሎች ያሉባት ሀገርም ናት። ይህም በቱሪስቶች ዘንድ ተመራጭ እንድትሆን አደርጓታል።
በ2030ም የአየር ንብረት ብክለትን ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ ካቀዱ 100 የአውሮፓ ህብረት ከተሞችም አንዷ ናት፡፡
ሁለተኛዋ የአውሮፓ አረንጓዴ ከተማ የሚል ስያሜ የተሰጣት የኖርዌይዋ ኦስሎ ናት። በዘይት እና በነዳጅ ምርት የምትተዳደርው ከተማዋ ጽዱ እና ለነዋሪዎቿ ሆነ ለጎብኝዎች ምቹ እንደሆነች ይነገርላታል።

በካይ ጋዘን ለመቀነስ በከተማዋ ከ270 በላይ የብስክሌት ማቆሚያዎች እና ከ5ሺ በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ መሙያ ጣቢያዎችን ገንብታለች። 63 በመቶ በደን የተሸፈነች ከተማ ነች።
በከተማዋ የሚገኘው ቱሪዘም ቢሮ እና የተለያዩ ድርጅቶች ጎብኚዎች የሚፈልጉትን መረጃ በማንኛውም ሰአት መስጠታቸው እንዲሁም ለመንቀሳቀስ ብሎም ለመኖሪያነት አመቺ መሆኑዋ ኦስሎን ተመራጭ አድርጓታል ።
በሶስተኛ ደረጃ ለአለም ምቹ ከተሞችን በመፍጠር የተጠቀሰችው የስኮትላንድዋ ግላስጎው ናት

ከ2016 ጀምሮ በየአመቱ 10ኛ ደረጃን ይዛ መቀጠል ችላለች። ከተማዋ የስሟ ትርጓሜ ሳይቀር ውድ አረንጓዴ ስፍራ ማለት እንድሆነ ይነገራል።
ግላስጎው በካይ ጋዛን ለመቀነስ በ2023 ወደ መሃል ከተማ የሚገቡ በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን ክፍያ ማስከፈል ጀምራለች በዚም ጎጂ ልቀትን ለመከላከል የቻለች መሆኑ ይነገርላታል።
ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የባትሪ ቻርጅ ጣቢያዎች፣ የብስክሌት ኪራዮችን እና አዳዲስ መንገዶችን ገንብታለች። በተጨማሪም በከተማዋ ከ90 በላይ ፓርኮች ይገኛሉ። ይህም በአለም ላይ በልምላሜዋ እንድትታወቅ እና በጎብኝዎች ዘንድ ተመራጭ መዳረሻ እንድትሆን አድርጓታል።
በአራተኛነት የተቀመጠችው ደግሞ በህንጻ ጥበቡዋ እና በወይን ምርቶ የምትታወቀው የፈረንሳይዋ Bordeaux ናት።

ከተማዋ የተሻለ ከተማ ለመሆን የምታደርገው ጥረት በግልጽ የሚታይ ሲሆን በዘመናዊ የባቡር አገልግሎቶች፣ የኤሌክትሪክ መጓጓዣዎች እና በሞተሮች ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ቀላል እና ምቹ ከተማ ስለመሆኗ ይነገራል።
በከተማዋ የሚመረቱ ምርቶችን በማቅረብ፣በህዝባዊ ዝግጅቶች ላይ የፕላስቲክ ምርቶችን ባለመሸጥ እና ተረፈ ምርቶችን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ዝናን አትርፋለች ።
ሪፖርቱ በአምስተኛነት ያስቀመጣት እ.ኤ.አ በ2017 የግሎባል ዴስቲኔሽን ሰስቴነብሊቲ ኢንዴክስ ደርጃን የተቀላቀለችው እና ከደቡብ ኮሪያ ከተሞች የመጀመሪያ የሆነችው ጎያንግ ናት።

ለተከታታይ አመታት በመሻሻል ላይ ያለች በመሆኗም ተሸላሚ ሆና ቆይታለች ።
የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን እና አረንጓዴ ኢኮኖሚን መገንባት ራዕይዋ አድርጋለች ።
በምታዘጋጃቸው ማናኛውም ሁነቶች እና የተለያዩ ዝግጅቶች የአየር ብክለትን ለመቆጣጠር በምታደርገው ጥረት በ2021 የISO ሽልማትን ማግኘት ችላለች ።
አሁን ላይ ኤግዚቢሽን ማዕከሎቹዋ የዝናብ ውሃን በማጠራቀም እና ማጣራት ለመታጠቢያ ቤት አገልግሎት፣ ለአትክልት ስፍራ እና ለኩሬነት ጥቅም ላይ ያወላሉ። ከ68 በላይ የመኪና ማቆሚያ ስፍራወች እና የህዝብ የሳይክል አገልግሎት በከተማዋ እንደልብ ይገኛሉ።
በ- የአብስራ ብርሃኑ
.












