፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 16 2016| NBC ETHIOPIA- በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ክፍለ ከተማ ጠሮ መስጊድ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በግንባታ ላይ ያለ የመኖሪያ ቤት ተደርምሶ በደረሰ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

የአዲስ አበባ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኤኤም ኤን በሰጡት መረጃ የግለሰብ መኖሪያ ቤት አፈርና ግንብ ተንዶ በደረሰው አደጋ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች በመኖሪያ ቤታቸው ተኝተው በነበሩበት ሌሊት 11 ሰዓት ላይ ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












