አዲስ አበባ | ሚያዚያ 05፣ 2016| NBC ETHIOPIA- የድርጅቶች መለያ አርማ ገላጭ፣ ለማስታወስ ቀላል ፣ ያልተወሳሰቡ እና ሰዎች በቀላሉ የሚያስታውሷዋቸው እንዲሆኑ ይጠበቃል።
በአለማችን ሰዎች የተለያዩ የቢዝነስ ምልክቶችን ባዩበት ቅጽበት በአርማዎቻቸው የሚለዩዋቸው ተቋማት በርካታ ናቸው።
እነዚህን አርማወች ለማሰራት የሚወጡ ወጪዎች ሀገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ ሀገራት አነጋጋሪ እየሆነ መቶል።
መዋለ ነዋይ ፈሰስ ተደርጎባቸው ከተሰሩ አርማወች ውስጥ ውድ የሚባሉትን ልንነግራቹ ወደድን
በአምስተኛነት የተቀመጠው በአውስትራሊያ የሚገኘው ግዙፍ ባንክ በምህጻረ ቃሉ anz ነው። ባንኩ ከተመሰርተበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ አርማዎችን ቀያይሯል።

በ2009 ይፋ ያደረገው አዲሱ ሎጎ M&C Saatchi በተባለ ግለሰብ ቀድሞ የነበርውን በማሻሻል የተነደፈ ሲሆን መለያ ምልክቱም የባንኩን ስም ሶስት የመጀመሪያ ፊደላት መሰርት አድርጎ የተነደፈ ነው፤
በአዲሱ ሎጎ ላይ የተጨመረው ከፊደላቱ በላይ ያለው ቅጠል መሰል አርማ ባንኩ በአውስትራሊያ፣ኒውዚላንድ እና እስያ የቢዝነስ መሰረቱን የዘረጋ መሆኑን የሚገልጽ ነው። ባንኩ አርማውን ለማሰራት 15 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ፈሰስ አድርጎበታል።
አራተኛው እና ከፍተኛ ወጭ ወቶበታል የተባለው ሎጎ በፈርንጆቹ 1967 የተመሰረትው እና ባለቤትነቱ የኖርዌይ የትራንስፖርት እና ኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር Posten Norge የተሰኘው የፖስታ ላኪ ድርጀት ነው።

ድርጅቱ እ.ኤ.አ በ2008 አሻሽሎ ይፋ ያደርገው እና አሁን እየተጠቀመበት ያለው መለያ ምልክቱ ቀለል ያለ እና ሊታወስ የሚችል ሆኖ ተሰርቷል፡፡
ምልክቱ ከላኪው ወደ ተቀባዩ ሲደርስ ያለውን ሀሳብ ለማሳየት እና Posten የሚለው ስም ደግሞ የኖርዌይ የፖስታ አገልግሎት የሚል ትርጉምን ያዘለ ነው። ይህንንም አርማ አሻሽሎ ለመስራት 55 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ከፍሎበታል።
አክሰንቸር የማማከር አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት ነው፣ ድርጅቱ አርማውን ለማሰራት በከፈለው ከፍተኛ የገንዘብ መጠን በሶስተኛ ደረጃ ተቀምጧል።

በ2001 ቀድሞ ይጠራበት ከነበርው ከአንደርሰን ኮንሰልቲንግ ወደ አክሰንቸር ስሙን መቀየሩን ተከትሎ ነው በ2017 አዲሱን አርማ ይፋ ያደረገው። አርማውም የድርጅቱን ሙሉ ስም በትንንሾቹ የእንግሊዘኛ ፊደላት የተጻፈበት እና በላዩ ላይ የይበልጣል ምልክትን የያዘ ነው።
የሎጎው ንድፈ ሀሳብም ድርጅቱ እድገት እና ልማትን ለማምጣት እንደሚሰራ ያመላክታል ተብሏል።ለዚም ንድፍ 100 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ወጪ ተደርጎበታል።
በአለም ላይ ትልቁ የነዳጅ ማዲያ ድርጅት ብሪቲሽ ፔትሮሊየም በፈረንጆቹ ሚሊኒየም መጀመሪያ ላይ ይፋ ያደርገው ሎጎ በአለም ላይ ሁለተኛው ውዱ ሎጎ አስብሎታል።

መለያ ምልክቱ አረንጓዴ እና ቢጫ ቀለምን እንደ ዋና ቀለሞች በመጠቀም የአካባቢን አረንጓዴንት ለመጠበቅ እና ለመንከባከብ የሚያደርገውን ጥረት የሚያሳይ ሃሳብ እንደያዘ የሚገልጽ ነው ተብሎለታል። እናም የድርጅቱ ሎጎ በ210 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተሰራ ነው፡፡
በአለማችን እስከዛሬ ለተሰሩ የተቋማት ንድፈ ሃሳቦች ተከፍሎ የማይታወቅ ክፍያን በመክፈል የአለም ውዱ አርማ በመሆን አንደኝነቱን የተቆናጠጠው የአሜሪካው ሶፍት ዌር ካምፓኒ ሳይማንቴክ ነው።

የአርማው ሃሳብ ቀጣይነትን እና መርጋጋትን የሚጠቁም ሲሆን ለደንበኞቹ የመተማመን እና የደህንነት ስሜት ይፈጥራል ነው የተባለው። በላዩ ላይ ያለው የራይት ምልክት የሚመጡ ጉዳዮች ሁሉ የተሳኩ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው።
ድርጅቱ በአርማው ላይ ላደርገው ማሻሻያ እና VeriSign የተባለውን ኩባኒያን ለመግዛት በአጠቃላይ 128 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ፈሰስ አድርጎበታል በዚም በአለም ላይ እስከዛሬ አቻ ያልተገኘለት ውዱ ሎጎ መሆን ችሏል።
በ-የአብስራ ብርሃኑ












