፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 04፣ 2016| NBC ETHIOPIA-የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፉን ያሳድጋል ብሎም የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ይጨምራል ያለውን አዲስ ስትራቴጂ መንደፉን አስታውቋል።
በአዲሱ ስትራቴጂ መሰረት በ2030 78% ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ይሆናሉ ያለ ሲሆን 96.2% በከተማና 72.3% በገጠር የሚኖሩ ዜጎች ናቸው።
ዘርፉን ለማዘመን ያግዛል በሚል ተስፋ የተጣለበት አዲሱ ስትራቴጂ ኢኮኖሚያዊ እድገትን፣ ስራ ፈጠራ፣ የከባቢ አየር ጥበቃ አስተዋጽኦ ከፍ ያለ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ከ2024 እስከ 2030 የሚቆየው ስትራቴጂውን በተመለከተ ለሚመለከታቸው የፌደራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ሃላፊዎች፤ የክልል ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊዎችና ለሚመለከታቸው አካላት ገለፃ ተደርጓል።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












