Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

አንጋፋው የቀድሞ ድምጻዊ ሙሉቀን መለሰ

April 12, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አዲስ አበባ | ሚያዚያ 04፣ 2016| NBC ETHIOPIA-በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ስማቸውን በጉልህ ማስፈር ከቻሉ የምን ጊዜም ተወዳጅ  ድምጻውያን መካከል አንዱ ነው፤ ምንም እንኳን  ሙዚቃን ካቆመና መንፈሳዊ ህይወትን መምራት ከጀመረ  ለግማሽ ምዕተ አመት የተጠጋ ጊዜያት ቢቆጠርም የሙዚቃ ስራዎቹ ልክ እንደ ትላንት ዛሬም በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነቱን እንደያዙ መዝለቅ ችለዋል፤ የቀድሞው ድምጻዊ ሙሉቀን መለሰ ፡፡

በ1946 ጎጃም ክፍለ ሀገር አነደድ ወረዳ ውስጥ ዳማ ኪዳነ ምህረት በምትባል መንደር የተወለደው ሙሉቀን መለስ ወላጅ እናቱን ያጣው ገና ልጅ ሳለ ነበር ፡፡ ለሙሉቀን እናቱ ሁሉ ነገሩ ነበሩ እሳቸውን ማጣት ክፉኛ የሀዘን ድባብ ውስጥ እንዲገባ እንዳደረገው በተደጋጋሚ ባደረገው ቃለምልልሶች ተናግሯል ፡፡ በእናቱ ሀዘን ሙሉቀን መጎዳቱን ያስታዋሉት አጎቱ በ 1958 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ይዘውት መጡ ፤ ኮልፌ ሰፈር ጳውሎስ ትምህርት ቤት ገብቶም ትምህርቱን ተከታትሏል ፤ ሙሉቀን የአጎቱ  ቤት ህይወት አሁንም በፈተና የተሞላ ነበር በተዳጋጋሚም ከአጎቱ ሚስት ጋር ይጋጭ ነበር ይህ ሁኔታና ሌሎችም ነገሮች ተደራርበው ምቾትን ስላልሰጡት ከአጎቱ ቤት ጠፍቶ በመውጣት ኮልፌ   አካባቢ በሚገኘውና የከንቲባ ዘውዴ ገብረህይወት ባለቤት ወ/ሮ ድርብወርቅ  በበላይ ጠባቂነት በሚመሩት  የልጆች ማሳደጊያ ሊገባ ችሏል ፡፡ በዚህ የህጻናት ማሳደጊያም ለአጭር ጊዜም ቢሆንም የተረጋጋ ህይወትን እንዲመራ አስችሎታል  ፡፡

የሙሉቀን መለሰ እና የሙዚቃ ትውውቅ የተጠነሰሰውም በዚህ ማደጎ ቤት አካባቢ በተከፈተ አንድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት እንደ ነበር ይነገራል ፤ ለስድስት ወራት ያክል በታዋቂው የሙዚቃ ሰው ተፈራ አቡነ ወልድ አማካኝነት የሙዚቃ ትምህርትን ተከታትሏል፡፡

ከህጻናት ማሳደጊያውም ከወጣ በኋላም በወቅቱ በደሙ ውስጥ ይዘዋወር የነበረውን ታላቅ የሙዚቃ ፍቅር በመዝፈን ለመወጣት እና ለነፍሱ እፎይታን ለመስጠት በርካታ ጥረቶችን አድርጓል ፡፡

ሙሉቀን መለሰ ከብዙ ድካም በኋላ በወቅቱ ታዋቂ በነበረውና ውቤ በረሃ አካባቢ በሚገኘው ፓትሪስ ሉሙምባ የምሽት ክለብ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ በሙዚቃ ስራ ውስጥ መሳተፍ ጀመረ፤ በአንድ ቃለ መጠይቁ ላይ በወቅቱ በምሽት ክለቡ  የተቀጠረበትን ግዜ ሲያስታውስ እንደዚህ ብሏል፤

አንድ ምሽት እኔ እና ጓደኞቼ ስንጫወት አመሸን እና ወደ ሶስት ሰዓት ላይ አንዱን ጓደኛቸውን ለመሸኘት እንሄዳለን፤ ደጃች ውቤ ሰፈር ስንደርስ የውቤ በርሀ ልዩ ልዩ ቀለማት መብራቶች በርተው ለአይን ይማርኩ ነበር፤ በጣም ተደንቄ ምንድን ነው ስል ጠየኩ፤ ይኸማ ‘ፈጣን ኦኬስትራ’ የሚጫወትበት ‘ፓትሪስ ሉሙምባ ናይት ክለብ’ ነው አሉን።

ፊት ለፊቱ ካለው ሱቅ በመሄድ፣ ወረቀት እና እስኪርቢቶ በመለምን ለክለቡ ባለቤት “ወይዘሮ አሰገደች አላምረው “ሥራ ይሰጡኝ ይሆን ወይ?” የሚል ደብዳቤን ጻፍኩ፤ በፍርሃት እየታገልን ገብተን ለኦኬስትራው መሪ ደብዳቤውን ሰጠሁት፤ አነበበውና ሳቀብኝ

“ምንድነው እሱ?” አሉ ወይዘሮ አሰገደች ከወዲያ ቁጭ ብለው።

ሰውየው ነገራቸው። ደብዳቤውን ተቀብለው አነበቡ።

“ፈትነው። ካለፈ ጥሩ … አለዚያም ሌላ ሥራ እሰጠዋለሁ” አሉ።

ያን ጊዜ እንደ ጥላሁን ገሰሰና እንደ ዓለማየሁ እሸቴ እያደረኩ እዘፍን ነበር። ባዶ እግሬን በቁምጣ ሱሪ መድረኩ ላይ ወጣሁና ‘ለእውነት እሞታለሁ፣ አልሳሳም ለነብሴ’ን እና ‘እንክርዳድ’ን ዘፈንኩ።

የናይት ክለቡ ሴቶች (በጣም ብዙ ናቸው) ዘፈኑን ወደዱልኝ እና ያን ጊዜውኑ አንድ አራት መቶ ብር የሚሆን አዋጡልኝ።

“በበነጋታው ካኪ ልብስ ተገዛልኝ፤ ሱፍ ልብስ ተለካሁ። ቢትልስ ጫማ አደረኩ … እግሬን ታጥቤ!” ።

እዚያው ክፍል ተሰጠኝ። ምግብም ከዚያው ነው። የዘፈን ሥራ ጀመርኩ።

ወደ ናይት ክለቡ የሚመጣው ሰው እየበዛ ሄደ። ወይዘሮ አሰገደች ኮንትራት (ውል) አስፈረሙኝ። እኔ ማታ ማታ ልዘፍን፣ እሳቸው በወር ዘጠና ብር ሊከፍሉኝ።

“ዘጠና ብር! ሚልየኔር የሆንኩ ነው የመሰለኝ!” ።

በ 13 አመት እድሜው ሙዚቃ ውስጥ የገባው ድምጻዊው ከተወሰኑ አመታት በኃላ በፖሊስ ኦርኬስትራ ውስጥ በመቀላቀል የምንጊዜም ተወዳጅ የሆኑ ‘እምቧይ ሎሚ መስሎ’፣ ‘የዘላለም እንቅልፍ’፣ ‘እናቴ ስትወልደኝ መቼ አማከረችኝ’፣ ‘ያ ልጅነት’፣ የተሰኙ እና ሌሎች በርካታ ተወዳጅ ሙዚቃዎችን ተጫውቷል።

ሙሉቀን መለሰ እስከ 1975 አመተ ምህረት ድረስ ባሉት አመታት ከሙላቱ አስታጥቄ፤ ከሮሃ፤ ዳህላክ እና ኢትዮ ስታረር ባንዶች ጋር በርካታ ጥኡመ ዜማዎችን ሲያደርስ ቆይቷል፡፡

በአንድ ወቅት ከሙዚቃ ሥራዎቹ መካከል የትኛውን አብልጦ እንደሚወድ የተጠየቀው ሙሉቀን ሁሉንም ሥራዎችቹን ዕኩል እንደሚያያቸው በመግለጽ በዜማ እና በዘፈን የተለዩ ናቸው የሚላቸውን ጠቅሶ ነበር።

“…በጣም የሚያረኩኝ…በዜማው እና በዘፈኑ…‘ሰውነቷ’ እና ‘ሆዴ ነው ጠላትሽ’…በሙዚቃ ጥራት እና ባሠራር ደግሞ፣ ሙላቱ አስታጥቄ ያቀነባበራቸው እና ከዳህላክ ባንድ ጋር የዘፈንኳቸው ‘ቼ በለው’ እና ‘ውቢት’” የተባሉትን ለእሱ ከሌሎቹ የተለዩ ነበር።

ከድምጻውያን አለማየሁ እሸቴ ፤ ሚኒሊክ ወስናቸውን ሂሩት በቀለ፤ ብዙነሽ በቀለ እና መሃሙድ አህመድ አድናቂ መሆኑንም ይናገራል፡፡

ሙሉቀን መለሰ በ17 አመታት የሙዚቃ ህይወት ቆይታ በግጥምና ዜማ ስራዎች የጎላ ተሳትፎ በማድረግ፤ የራሱን አይነት ስልት ይዞ በመምጣት ለብዙ ድምጻያን መነሻ በመሆን ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ትልቅ አበርክቶትን ያሳረፈው ድምጻዊው በ 1980ዎቹ ሙሉ ለሙሉ ከሙዚቃ ህይወት በመውጣት የመንፈሳዊ ስራዎች ላይ መሳተፍ ጀምረ፡፡

ከዛን ጊዜ አንስቶ መኖሪያው ባደረጋት ሀገረ አሜሪካ  በመሆን ለአራት አስርት አመታት ለወንጌላውያን አማኞች የመዝሙር ስራዎችን ያደርስ ነበር፡፡

ጋሽ ስብሃት ገብረ እግዚአብሄር በአንድ ወቅት በፅሁፎቹ ያሞገሰው፤ የብዙ ኢትዮጵያውያን የወጣትንት ትውስታ የሆነው፤ እስካሁንም ድረስ ላሉ ድምጻያን ምሳሌ የሆኑ ስራዎችን ያበረከተው የቀድሞ ድማፃዊ እና ዘማሪ  ሙሉቀን መለሰ  ለረጅም ጊዜ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በተወለደ በ70 ዓመቱ ሚያዚያ 1 ቀን 2016 ዓ.ም  ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል :: የቀብር ስነስረአቱም በነገው እለት አርብ ሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም  በአሜሪካን ሀገር በዋሽንግተን ዲሲ ይፈጸማል ፡፡ ሙሉቀን መለሰ ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት ነበር ፡፡  ኤን ቢሲ ኢትዮጵያ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል፡፡

በ–አብስራ ሚሊዮን

ShareTweetShare
Previous Post

የፍልስጤም የአባልነት ጉዳይ

Next Post

የአለማችን ውድ ሎጎዎች

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የአለማችን ውድ ሎጎዎች

የአለማችን ውድ ሎጎዎች

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉለሌ ክፍለከተማ የተገነቡ የተቀናጁ ልማት ስራዎችን አስመረቁ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉለሌ ክፍለከተማ የተገነቡ የተቀናጁ ልማት ስራዎችን አስመረቁ

የማይግሬን ራስምታትን ለማስታገስ

የማይግሬን ራስምታትን ለማስታገስ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?