አዲስ አበባ | መጋቢት 27፣ 2016| NBC ETHIOPIA-በፈረንጆቹ ሚያዚያ 15፤ 2024 ተፈጻሚ ይሆናል የተባለው ማዕቀብ 164 የሩሲያ ሸቀጦች ወደ ጃፓን እንዳይገቡ እንደሚከለክል የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሚኒስትር አስታውቋል፡፡

ወደ ጃፓን እንዳይገቡ ከተከለከሉት የሩሲያ ምርቶች መካከል የሞተር ዘይቶች ፤ የሊቲየም ባትሪዎች፤ የጋዝ ማስተላለፊያ ብረቶች፤ የመዋቢያ ቁሳቁሶች እና ሌሎች ሩሲያ ሰራሽ ምርቶች ወደ ጃፓን እንዳይገቡ መከልከላቸው ተገልጿል፡፡
ሩሲያ በበኩሏ ጃፓን የጣለችው ማዕቀብ መሰረት የሌለው እና የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የሚያጠለሽ ድርጊት ነው ስትል ተችተዋለች፡፡ ዘገባው የታስ ነው ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












