፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 27፣ 2016| NBC ETHIOPIA-ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ1 ነጥብ 72 ቢሊዮን ዶላር የድጋፍና ብድር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
-በሀገር አቀፍ ደረጃ በ850 ወረዳዎች የሀገራዊ ምክክር የተሳታፊ ልየታ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡
-በመዲናዋ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ለመቀነስ የሚያስችል 96 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የዝቅተኛ መስመር መልሶ ግንባታ ሥራ ተከናወነ::
-በ2ኛ ዙር ወደ ሀገር ለሚገቡ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን አቀባበል ተደረገ፡፡
-የፊቼ ጨምበላላ በዓል በሐዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡
-ለመጪው የኢድ አልፈጥር በዓል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
-በካፋ ዞን በጊምቦ ወረዳ ቢጣ ጨጋ ቀበሌ ልዩ ስፍራው ዳራ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የጭነት ተሸከርካሪ ከባጃጅ ጋር በመጋጨታቸው የአምስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡
-ህገ-ወጥ የሰዎችን ዝውውር ለመግታት ህጋዊ የሆኑ አማራጮች ተዘርግተው ዜጎች ወደ ሌሎች ሀገራት እንዲሄዱ እየተደረገ መሆኑን የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ገለፀ።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












