፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 25፣ 2016| NBC ETHIOPIA-ታይዋን በ25 ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ከፍተኛ ርዕደ መሬት አደጋ መመታቷ ተገለጸ
ርዕደ መሬቱ በሬክተር ስኬል 7.4 የሚለካ ሲሆን አራት ሰዎች ህይወታቸውን ሲያልፍ 736 የሚሆኑ ቆስለዋል ተብሏል ፡፡
በርዕደ-መሬቱ ምክንያት ሱናሚ ሊነሳ ይችላል የሚል የማስጠንቀቂያ መልዕክት ለደሴቷ እና በአቅራቢያው ለሚገኙ ነዋሪዎች መተላለፉን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውዋል ።

በመዲናዋ ታይፔይ መኖሪያ ቤቶች ፈራርሰው ሰዎችን የማዳን ሥራ እየተከናወነ እንደሆና የከተማዋ ነዋሪዎች ከቤታቸው እንዲሁም ከትምህርት ቤት እንዲወጡ እየተደረገ ነው እንደሚገኝ ተዘግቧል፡፡
የጎረቤት ሀገር ጃፓን ባለሥልጣናት በበኩላቸው ታይዋንን ከመታው ርዕደ-መሬት በኋላ ነዋሪዎች በተጠንቀቅ እንዲጠብቁ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












