፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 10፣ 2016| NBC ETHIOPIA -የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ እና የስዊዘርላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢግናስዮ ካሲስ በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ የስዊዘርላንድ ኤምባሲ ለሚያስገነባው አዲሱ የግንባታ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡
-የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ባለፉት ስድስት ወራት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች 20 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።
-የቃሊቲ – ቡልቡላ – ቅሊንጦ አደባባይ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በሁሉም አቅጣጫ ለትራፊክ ክፍት ሆነ፡፡
-6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 18ኛ መደበኛ ስብሰባው ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ /ማሻሻያ/ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር ዕይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡
-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በዓለም ባንክ ፋይናንስ በሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ላይ የኢንጂነሪንግ የማማከር ሥራዎችን በራሱ አቅም እንዲሠራ ከባንኩ ፈቃድ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡
-አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአምስት ዓመቱን ስትራቴጂ ለማሳካት ከግሉ ዘርፍ ጋር በትብብር እንደሚሰራ ገለፀ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












