፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 05፣ 2016| NBC ETHIOPIA -በቻይና የአሳ ማጥመጃ ጀልባ ሰጥሞ የሰዎች ህይወትን ቀጠፈ፡፡አደጋው የደረሰው በምስራቅ ቻይና ፉጃን ግዛት ነው ተብሏል፡፡
የአካባቢው የባህር ሀይል ባለስልጣን እንደገለጸው፤ በጀልባዋ ከነበሩት ስድስት ሰዎች ውስጥ፤ ሁለቱ ሲሞቱ፤ ሌሎች ሁለት ሰዎች ደብዛቸው ጠፍቷል ፡፡ በጀልባ ውስጥ የነበሩ ሁለት ሰዎች በህይወት መተርፋቸውም ተነግሯል ፡፡ ጀልባዋ ከአለት ጋር ተጋጭታ አደጋው ደርሶባታል ፡፡
እንደ ሲ ጅ ቲ ኤን ዘገባ ሄሊኮፕተሮችና የነፍስ አድን ሰራተኞች የጠፉትን ሰዎች በማፈላለግ ላይ ናቸው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












