፨ ፨ ፨ ፨ ፨
በዓለማችን ከፍተኛ የተጠቃሚ ቁጥር ካላቸው መተግበሪያዎች መካከል ቲክ ቶክ ከቀዳሚዎቹ ተርታ ይቀመጣል፡፡
የማህበራዊ የትስስር ገጽ መተግበሪያው ቲክ ቶክ በአለም ዙሪያ ያሉት ተጠቃሚዎች ቁጥር በፈረንጆቹ 2023 1 ነጥብ 92 ቢሊየንን ተሻግሯል፡፡
በየቀኑ ከ750 ሚሊየን የሚልቁ ሰዎች የሚጠቀሙት ይህ የማህበራዊ የትስስር ገጽ 50 ቢሊየን ዶላር ዋጋ እንዳለው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡በ40 ሀገራትም ጥቅም ላይ የዋለ ቁጥር አንድ መተግበሪያም ነው፡፡
ይህ የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያ በተለይም በአሜሪካ ከቅርብ አመታት ጀምሮ ተደጋጋሚ ወቀሳዎችና ማስጠንቀቂያዎች እየደረሱት ይገኛል፡፡
የአሜሪካ ምክር ቤት መተግበሪያውን በሀገሪቱ ውስጥ ሊያግደው እንደሚችል ማስጠንቀቂያዎችን ሲሰጥ የቆየ ሲሆን በጉዳዩም ላይ ድምጽ ለመስጠት ቀጠሮ ይዟል፡፡

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ሹ ቻው ከአሜሪካ የኮንግረስ አባላት ጋር ለ11 ሰአታት ስብሰባዎችን ለማድግ ሞክሯል።
ስራ አስፈጻሚው ቲክ ቶክን ለሚቃወሙ ሃሳቦች የተለሰጡ አሉታዊ ምላሾችን የያዙ ደብዳቤዎችን ለሕግ አውጭዎቹ አቅርቧል። የትኛውም በቲክ ቶክ ላይ የሚደረጉ እግዶች 5 ሚሊዮን በመተግበሪያው ላይ የተመሰረቱ ቢዝነሶችን ነው የሚጎዳው ሲሉ ስራ አስፈጻሚው መከራከሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
ሲኤን ኤን እያስነበበ በሚገኘው ዘገባ ይህ እግድ በህግ አውጪዎቹ ከጸደቀ 4 ሚሊዮን ተከታይ ያሉት እና በትምህርት በጤና በሴቶች ጤና ላይ ትምህርት የሚሰጠው የOkamoto የቲክቶክ ገጽ ላይ የሚፈጥረው አሉታዊ ድባቡ የላቀ ይሆናል ይላል፣ Okamoto በትምህርት በጾታ እኩልነት እና በሴቶች ጤና ላይ መረጃን የሚሰጥ የግል የቲክቶክ ገጽ ነው፡፡
ኦካሞቶ ኢሲያ አሜሪካዊ ዜግነት ያለው ነው ለሲኤን ኤን እንደተናገረው ቲክ ቶክ ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ጋር ግንኙነት አለው በሚል ጥርጣሬ እና ከንቱ ጥላቻ ነው ይህን ያህል ተጽእኖ እየተደረገበት የሚገኘው ብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ቲክ ቶክ በአሜሪካ ውስጥ 102 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች እንዳሉት የሚነገር ሲሆን ይህም የተጠቃሚ ቁጥር በ2027 121 ነጥብ 1 ሚሊዮን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እ.ኤ.አ ከሚያዚያ 2023 ጀምሮ ከሀምሳ ግዛቶች ቢያንስ 34 ግዛቶች ላይ መንግስት በሰጣቸው መገልገያዎች TikTokን በሚጠቀሙ የመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ሰራተኞችና ተቋራጮች ላይ እገዳ ወጥቷል፡፡
እገዳው የመንግስት ሰራተኞች በመንግስት ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን ብቻ የሚመለከት ሲሆን ሌላው ማህበረሰብ ግን መተግበሪያውን በግል መሳሪያው ላይ እንዳይጠቀም አይከለክልም።
አሜሪካ የቲክቶክን መተግበሪያ ለማገድ የወሰነችው የቲክቶክ ተጠቃሚዎችን መረጃ ለቻይና መንግስት አሳልፎ እየሰጠ ነው በሚል ስጋት ሲሆን ድርጅቱ ግን መረጃውን አጥብቆ ሲቃወም ቆይቷል፡፡
የቲክ ቶክ መተግበሪያ እግድ ከጸደቀ 5 ሚሊዮን በሚደርሱ በንግድ ላይ የሚገኙ ሰዎችን በቀጥታ እንደሚጎዳ ተጠቁሟል፡፡
በጉዳዩ ላይ በሀገሪቱ ዜጎች ዘንድ የተለያዩ አስተያየቶችን እየሰጡ ሲሆን ስራዎቻቸውን ለማስኬድ ቲክ ቶክ ከፍተኛ እገዛ እያደረገላቸው እንደሚገኝ ይነገራሉ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ለማህበራዊ ህይወታቸውም የራሱን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል የሚሉት አስተያየት ሰጪዎቹ አገልግሎቱን እንዲቀጥል ሊፈቀድለት ይገባል ሲሉ ሀሳባቸውን ይሰጣሉ፡፡
የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያው ከአሜሪካ ባሻገር የተለያዩ ሀገራት እግድ የወጣበት ሲሆን ከነዚህም ሀገራት መካከል አፍጋኒስታን ተጠቃሽ ነች፡፡
ሀገሪቱ መተግበሪያውን ያገደው በ2022 ሲሆን የሚቀርቡ ይዘቶች “ከኢስላማዊ ህጎች ጋር አይጣጣሙም” በሚል ነው፡፡
አውስትራሊያ ሌላኛዋ በቲክ ቶክ ላይ እግድ ያስተላለፈች ሀገር ስትሆን በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ የተነሱ የደህንነት ስጋቶችን በመጥቀስ መተግበሪያው ከሁሉም የፌደራል መንግስት ባለቤትነት ከሚያዙ መሳሪያዎች ታግዷል።
ከመንግስት ባለስልጣናት የስራ ስልኮች ቲክ ቶክን መጠቀም ያገደችው የቤልጂየም ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ዴክሩ “የዋህ መሆን አንችልም፡ ቲክ ቶክ በአሁኑ ጊዜ ከቻይና የስለላ አገልግሎቶች ጋር የመተባበር ለቻይና የሚሰራ ኩባንያ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ካናዳም ብትሆን ቲክቶክን ከሁሉም የመንግስት ተንቀሳቃሽ መሳሪያዎች አግዳለች።
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን እና ኔቶን ጨምሮ አለም አቀፍ የመንግስት አካላት ሰራተኞቻቸው በስራ ስልኮቻቸው ላይ ቲክ ቶክን እንዳይጠቀሙ ከልክለዋል፡፡
በ-አክረም ኑርያ