፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡
አዲስ አበባ | መጋቢት 03፣ 2016| NBC ETHIOPIA -ቫቲካን በዩክሬን ሰላም እንዲመጣ ሩሲያ ወረራዋን ማቆም አለባት ስትል መልዕክት ማስተላለፏ ተገለጸ፡፡
ቫቲካን በመልዕክቷ እንዳስተላለፈችው ወደ ውይይት ለመግባት እና በሁለቱ ሀገራት ያለውን ጦርነት ወደ ሰላም ለመቀየር የመጀመሪያው ሁኔታ ሩሲያ ጥቃቷን ማቆም ይኖርበታል ፡፡
የሮማን ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ የድርድር ሀሳብ ቢያቀርቡም በዩክሬን በኩል ተቃውሞ ቀርቦባቸዋል ተብሏል ፡፡ ሊቀ ጳጳሱ ባለፉት ቀናት ዩክሬን ነጭ ባንዲራ በማሳየት ከሩሲያ ጋር ለድርድር እንድትቀመጥ ሀሳብ ማንሳታቸው ይታወሳል፡፡ ዘገባው የሮይተርስ ነው ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












