አዲስ አበባ | የካቲት 30፣ 2016| NBC ETHIOPIA – የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በሀገር ዉስጥና በመላው ዓለም ለሚገኙ ምእመናን አብይ ጾምን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችው መልዕእት አስተላልፈዋል፡፡
አብይ ጾም በጥንት ጊዜ ሰው በኃጢአት የወደቀበትን ምክንያት እንዲሁም ሰው ኃጢአትንና ዲያብሎስን እንዴት እንደሚያሸንፍ ጌታችን እኛን ያስተማረበት ነው ብለዋል አቡነ ማትያስ፡፡
ብጹነታቸው ጌታችን የአሸናፊነት መንገድ በቃልና በተግበር አስተምሮናል፤ሰይጣን የሚሸነፍበት ስልት በሌላ ሳይሆን፣ሥጋዊ መጎምጀትን ከአእምሮአችን አውጥተን በመወርወር ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ስጋችን በፍቅረ ንዋይ፤በሥልጣን፣በዝሙት እንዲሁም በተለያዩ ሥጋዊ ምኞት ሊጎመጅ ይችላል፤ ያን ጊዜ ሰይጣን እነሱን እንድንፈፅም ሊገፋፋን እንደቆመ ስናስብ ”አንተ ሰይጣን ከኃላዬ ሂድ‘‘ እንበለው ፤ ያስጎመጁን ነገሮችን በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር ከኅሊናችን አውጥተን በመጣል ማለፍ አለብንም ብለዋል፡፡
ጾም ማለት ከእህልና እንስሳት ዉጤቶችን ከመመገብ መከልከል ብቻ አይደለም፤ የእንስሳት ውጤት የሆኑትን ላለመመገብ ከምንወስደው በላይ እኩያት ፍትወታትንና ኃጣውእን ላለማስተናገድ በቁርጥ መወሰን ይጠበቅብናል ሲሉ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ መልዕክታቸውምአስተላልፈዋል፡፡
በጾሙምመገዳደልን፣መጣላትን፣መገፋፋትን በመተው ዲያብሎስን ማሸነፍ ይገባል ብለዋል፡፡
ዲያብሎስን የምናሸነፈው እርስ በርሳችን ይቅር ስንባባል፤ለሰላምና አንድነት፣ለፍቅር ስንቆም መሆኑን በማንሳት ጾማችን በእግዛብሔር ተቀባይነት የሚኖረው የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው ተመልሰው ሰላማዊ ኑሮ መኖር ሲችሉ፣ የተራቡት ሲደገፉ፣ፍትህ ያጡት ፍትህ ሲያገኙ ነው ብለዋል፡፡
በአብይ ጾም ሁሉም ኢትዮጵያዊ የቁርስ በጀቱን ለተራቡ ወገኖች በመለገስ ወገኖቹን ከረሃብ ከሞት እንዲታግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን አስተላልፋለች፡፡
በ-ሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












