አዲስ አበባ | የካቲት 26፣ 2016| NBC ETHIOPIA -የ2016 የሀጅ ጉዞ ምዝገባ የካቲት 27/2016 ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረ ቢሆንም የተመዝጋቢዎች ቁጥር በታሰበው የጊዜ ገደብ ባለ መጠናቀቁ ምዝገባው እንዲራዘም መደረጉን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ::

የጠቅላይ ም/ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሼኽ አብዱል አዚዝ ሼኽ አብዱል ወሊ የዘንድሮው የሀጅ ምዝገባ ከተያዘው እቅድ አንፃር የተመዘገበው ቁጥር 80 በመቶ ያህሉ እንደሆነ ገልፀው የአመቱ ኮታ እስኪሞላ ድረስ ምዝገባ እንዲራዘም የሳኡዲ መንግስት መፍቀዱን አስረድተዋል::
ኢትዮጵያን ጨምሮ የሀጅ ምዝገባን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ላላጠናቀቁ ከ100 በላይ ሀገራት ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠ መገለፁ አይዝነጋም::
በ-አክረም ኑርያ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












