፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡
አዲስ አበባ | የካቲት 26፣ 2016| NBC ETHIOPIA -አሜሪካ የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ኢመርሰን ምናንጋግዋን፣ ባለቤታቸውን እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን በሙስና እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ ተሳትፈዋል በሚል ማዕቀብ ጣለች።
-ሱዳን ወደ አፍሪካ ሕብረት ለመመለስ ያስችላል ያለችውን ቅድመ ሁኔታ አቀረበች::
-ከሳምንት በፊት በሰሜናዊ ቡርኪናፋሶ በሚገኙ ሶስት መንደሮች ላይ በተፈፀመ ጥቃት ወደ 170 የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ አቃቤ ህግ ገልፀዋል፡፡
-ፈረንሳይ የጽንስ ማስወረድ መብትን ህገመንግስታዊ መብት አድርጋ አጸደቀች ይህም በህገመንግስቷ ውስጥ በማካተት ከዓለም የመጀመሪያዋ ሀገር ያደርጋታል።
-የቀድሞው ትዊተር (ኤክስ) የተሰኘው ማህበራዊ ትስስር ገጽ በአውሮፓ ሕብረት አዲስ ገደቦች ሊጣሉበት እንደሚችል ተገለጸ፡፡
-በጋዛ ቅዱሱ የረመዳን ወር ከመግባቱ በፊት በእስራኤል እና ሃማስ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የመደረሱ እድል ጠባብ መሆኑ ተገልጿል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












