አዲስ አበባ | የካቲት 15፣ 2016| NBC ETHIOPIA -ሀገራዊ አለመግባባቶችን እና ችግሮችን በምክክር ለመፍታት እንዲሁም የምክክሩ ቀጣይ ሂደት የተሳካ ለማድረግ የተለያዩ መድረኮች እያተከናወኑ ናቸው።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በአገር ውስጥ የሚታዩ አለመግባባቶች በጦርነት ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ ጉዳዮችን ወደ ጠረጴዛ በማምጣት በምክክር መፍታት እንደሚገባ አንስተዋል።
ኮሚሽኑን ሀገራዊ ምክክሮችን ለማካሄድ የተሳታፊዎች ልየታ የማከናወን ስራውን ከትግራይ ክልል ወጪ እንዳከናወነ ተገልጿል።
በቀጣይ ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው አካላት በመሆን አጀንዳ ልየት እንደሚደረግም ተነስቷል።
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ተቋቁሞ ስራውን ማከናወን ከጀመረ ሁለት ዓመታትን አስቆጥሯል።
በ-ሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












