Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ (አባ ጠና)

February 22, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አዲስ አበባ | የካቲት 14፣ 2016| NBC ETHIOPIA -አድዋ  የመስዋዕትነት ጮራ ነው፡፡ በቅኝ ግዛት ቀንበር ስር ለነበሩ ለመላው ጥቁር ህዝቦች ታላቅ መነቃቃትን የፈጠረ፤ በጦር ሜዳ ላይ ነጮች በፍጹም በጥቁሮች አይሸነፉም የሚለውን የተሳሳተ አመለካከት አፈር ድሜ ያስበላ አኩሪ የነጻነት የተጋድሎ ታሪክ ነው… አድዋ፡፡

በአድዋ ጦርነት ላይ ከ120 ሺህ በላይ ገበሬዎች በውጊያው ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመጡ አገረ ገዢዎችና የጦር አዛዦች በመካከላቸው ያለውን ቅራኔ ወደ ጎን በመግፋት አንድ ሆነው ለአንድ አላማ ጎን ለጎን ተሰልፈዋል፡፡

ንጉስ ተክለሀይማኖት ተሰማ ጎሹ (አባ ጠና) በአድዋ ጦርነት ላይ ታላቅ ተጋድሎን ከፈጸሙ ታዋቂ የኢትዮጵያ የጦር መሪዎች መካከል አንዱ ናቸው፡፡

ንጉሥ ተክለሀይማኖት ከአባታቸው ተሰማ ጎሹ እና ከእናታቸው ምዕላድ ነገዷ በ1843 ዓ.ም ጎጃም ውስጥ እንደተወለዱ የተለያዩ ጸሀፍቶች በጽሁፎቻቸው ገልጸዋል፡፡  

ተክለኢየሱስ ዋቅጅራ “የኢትዮጵያ ታሪክ” በተሰኘው መጽሃፋቸው ንጉሱ ወደ ስልጣን የመጡት በአጼ ዮሐንስ ዘመነ መንግስት ጥር 13 ቀን 1873 ዓ.ም በደብረ ታቦር ከተማ ‹‹ንጉሠ ከፋ ወጎጃም›› ተብለዉ የሸዋው ንጉስ ምኒልክ በተገኙበት ነው ይሉናል፡፡

ንጉሥ ተክለሀይማኖት አብዛኛው ህይወታቸው በጦርነት የተሞላ ነው፡፡ ራስም፣ ንጉስም ሆነው በርካታ ፈተናዎች አስተናግደዋል፡፡

ራስ እያሉ ከጎጃም የስልጣን ተቀናቃኞቻቸው እንዲሁም ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ተፋልመዋል፡፡ ጠላት ድንበር ጥሶ የኢትዮጵያን መሬት ለመውረር ያደረጋቸውን ሙከራዎች ለመቀልበስ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ጠላትን ተፋልመዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ በግንበር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ፡፡

የመጀመሪያው ጦርነት የሱዳን ደርቡሾች የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው ጥር 10 ቀን 1880 ዓ/ም ጎንደር ድረስ በመግባት ቤተክርስቲያን አቃጥለው ቀሳውስቱን ሲገሉ በወቅቱ አጼ ዮሐንስ አስመራ ነበሩ፡፡ ይህንን የሰሙት ንጉስ ተክለሀይማኖት አንድ መቶ ሺህ ሰራዊታቸውን ይዘው በመሄድ ደርቡሾች ላይ ከፍተኛ ድል አስመዝግበዋል፡፡ በወቅቱ ለጦርነቱ እንዲህም ተብሎ ተገጥሞ ነበር ይባላል፦

“ተከተልኸኝ ብዬ ዞሬ ዞሬ ሳይ፣

ወይ ጥጋብ ወይ ኩራት ጎንደር ቀረህ ወይ?

ወገራ አሳላፊ ደንቢያ እንጀራ ጣይ፣

ተበላህ ጎንደሬ አትነሳም ወይ?”

ኢጣሊያ ከውጫሌ ውል ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ወደ ውጥረት በገባችበት ዘመን ጦሩዋን ከጠረፋማ የባህር ዳርቻዎች በጥልቀት ወደ ኢትዮጰያ መሬቶች በመግባት አንዳንድ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ቦታዎችን በማን አለብኝነት መቆጣጠር ጀመረች፡፡

በወቅቱ ኢትዮጵያ ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሄ ለማፈላለግ በተደጋጋሚ መልዕክተኞችን ልካ ነበር፡፡ ሆኖም ግን የወራሪው ሀይል አላማ ሌላ ነውና በድርጊቱ ገፋበት፡፡ በ1887 ዓ.ም በጄኔራል ኦረሬ የሚመራው የኢጣሊያ ጦር ወደ ኢትዮጵያ በመግባት አድዋን ተቆጣጠር፡፡

ጥቅምት 2 ቀን 1888 ዓ.ም አፄ ምኒልክ የክተት አዋጅ በማወጅ አቅም ያለው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ውጫሌ ላይ እንዲከት አዘዙ፡፡ በፍጥነት የተሰባሰበው ጦርም ወደ ወረኢሉ ተመመ፡፡

ኢጣሊያኖች ጦርነቱ አይቀሬ መሆኑ በመገንዘባቸውም የየአካባቢው ገዚዎችን በመሸምገል ወደ ግንባር እንዳይሄዱ ጎትጉተዋል፡፡ ሆኖም ግን አብዛኛዎቹ አገራቸውን አሳልፈው አልሰጡም፡፡

አፄ ምኒልክ ወደ አድዋ ከመዝመታቸው በፊት ጣልያን ብዙ መኳንንቶችን ጥላቻ እንዲዘራባቸው ጥረት ሲያደርግ፤ አውግስቶ ሳልምቢኒ ጎጃም ዉስጥ ተቀምጦ የንጉስ ተክለሃይማኖት አጋዥ በመመስል የኢጣሊያንን ጦር ቢደግፉ በአጼ ምኒልክ ቦታ እሳቸው እንዲቀመጡ እንደሚያደርግ ሲወተውት ቆይቶ ነበር፡፡  

ንጉስ ተክለሃይማኖት ግን ጉዳዩን ችላ ብለው የክተት ጥሪውን ተቀብለው፤ ከ3 ሺህ በላይ ሰራዊት ይዘው ወደ አድዋ ገስግሰዋል፡፡ ንጉስ ተክለሃይማኖት ከአድዋ ጦርነት ጋር በተያያዘ ደማቅ ታሪክ አላቸው፡፡

እንደ ቤርክሊን ገለጻ ከሆነ ደግሞ ከጎጃም በአጠቃላይ 20 ሺህ ህዝብ የዘመተ ሲሆን፣ ፈረሰኛው 8 ሺህ፣ የጦር መሣሪያ የያዘ 11 ሺህ፣ ተከታይ 2 ሺህ ነበር ይላል ቤርክሊን አድዋን አስመልክቶ በፃፈው ፅሁፉ፡፡

መኳንንቶቹ ለጦርነት ዘመቻው ሰራዊታቸውን እየያዙ ወደአፄ ምኒልክ ሲያቀኑ ንጉስ ተክለሃይማኖት ዘግይተውም ቢሆን ታህሳስ 15 በበጌምድር በኩል አድርገው ከንጉሱ ጋር ተገናኝተዋል፡፡

በአገር ውስጥ በነበረው የስልጣን ሽኩቻ ንጉስ ተክለሃይማኖት ከአፄ ምኒልክ ጋር ቅራኔ ቢኖራቸውም በአገር ጉዳይ ወደ ኋላ አይሉምና በአንድ ላይ ቆመዋል፡፡

እንደሌሎቹ የጦር መሪዎች ሰራዊታቸውን አስተባብረው ስንቅ ከማዘጋጀት አንስቶ ጦርነቱን በመዋጋት ለድሉ መገኘት ሚናቸው የላቀ ነው፡፡

ንጉስ ተክለሃይማኖት ራስ አዳል ተሰማ ተብለው ከ1861-1872 ዓ/ም፤ ንጉሥ ተክለ ሀይማኖት ተብለው ከ1873-1893 ዓ/ም በድምሩ ለ32 ዓመት ጎጃምን አስተዳድረዋል፡፡እኚህ ጀግና ጥር 3 ቀን በ1893 ዓ.ም ከዚህች አለም በሞት ተለይተዋል፡፡

በ-ሰላም ይልማ

ShareTweetShare
Previous Post

በቬንዙላ የማዕድን ማውጫ ላይ የደረሰ አደጋ

Next Post

15ተኛው ከተማ አቀፍ የኪነ -ጥበብ ፌስቲቫል መካሄድ ጀመረ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
6
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
6
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
13
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
50
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
36
Next Post
15ተኛው ከተማ አቀፍ የኪነ -ጥበብ ፌስቲቫል መካሄድ ጀመረ

15ተኛው ከተማ አቀፍ የኪነ -ጥበብ ፌስቲቫል መካሄድ ጀመረ

ራስአባተቧያለውንጉሱ (አባ ይትረፍ)

ራስአባተቧያለውንጉሱ (አባ ይትረፍ)

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ከምሁራን ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ከምሁራን ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?