አዲስ አበባ | የካቲት 01፤ 2016| NBC ETHIOPIA -ጉምሩክ ኮሚሽን የኤሌክትሮኒክስ ካርጎ ትራኪንግ ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ የሀገሪቱን የንግድ ተወዳዳሪነት ለማሻሻል አዲስ ስርዓት ሊዘረጋ መሆኑን አስታውቋል።
በዛሬው እለት የተዋወቀው ቴክኖሎጂው የንግዱ ማህበረሰብ የጭነቱን ደህንነትና የደረሰበትን ቦታ ለማወቅ ያስችለዋል ተብሏል።
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን እውን ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የገለፁት የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ
የሀገሪቱ የካርጎ ስርዓት ደህንነትና ጥራቱን የጠበቀ እንዳይሆን ያደረጉ በርካታ ማነቆዎች መኖራቸውን ገልጸዋል።
በመሆኑም ቴክኖሎጂው ኮንትሮባንድን ጨምሮ በዘርፉ የሚስተዋሉትን ችግሮች ለመቅረፍ ያግዛል ተብሏል።
ባለቤትነቱ የጉምሩክ ኮሚሸን የሆነው ቴክኖሎጂው የበለፀገው በኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ነው። አዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ የማማከሩን ስራ ሰርቷል።
ቴክኖሎጂውንና አጠቃላይ የሀገሪቱን የኤሌክትሮኒክ ካርጎ ትራኪንግ ስርዓት በተመለከተ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ውይይት እየተደረገ ነው።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












