አዲስ አበባ | የካቲት 01፤ 2016| NBC ETHIOPIA -ፍቅረኛውን ገድሎ ከአሜሪካ ሸሽቶ በኬንያ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው ግለሰብ ከፖሊስ ማምለጡ ተነገረ።

የ41 ዓመቱ ኬልቪን ካንጌቴ በመዲናዋ ናይሮቢ ከሚገኝ አንድ የምሽት ክበብ ሲወጣም ነበር ባለፈው ሳምንት በቁጥጥር ስር የዋለው።
የኬንያ ፍርድ ቤት ግለሰቡ ለአሜሪካ ተላልፎ እስኪሰጥም ድረስ ለ30 ቀናት በቁጥጥር ስር እንዲቆይ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር።
ግለሰቡ ጥቅምት ወር ላይ የሴት ጓደኛውን ከገደለ በኋላ በቦስተን ሎጋን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሚገኝ ስፍራ በመኪና ውስጥ አስከሬኗን ጥሏት እንደሸሸ ባለስልጣናቱ ተናግረዋል። ከዚያም ወደ ትውልድ አገሩ ኬንያም ሸሽቷል ተብሏል። ግለሰቡ በቀረበበት ክስ ላይ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም።
ግለሰቡ ተይዞበት ከነበረው የናይሮቢ የፖሊስ ጣቢያ ወጥቶም በህዝብ ማመላለሻ ተሽካርካሪ ተሳፍሮ መሄዱን ፖሊስ አሳውቋል፡፡
ግለሰቡ ከማምለጡ በፊት አግኝተውታል የተባሉ በስራ ላይ የነበሩ አራት ፖሊሶች እንዲሁም ጠበቃው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የናይሮቢ የፖሊስ ኮማንደር አደምሰን ቡንጂ ገልጸዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv