አዲስ አበባ | ጥር 30፤ 2016| NBC ETHIOPIA -ታጣቂ ቡድኖች በምስራቃዊ ኮንጎ ጋኦማ ከተማ በሚኖሩ ሰዎች ላይ ባደረሱት ጥቃት ነዎሪዎች አካባቢያቸውን ጥለው እየተሰደዱ ነው ተባለ፡፡
ኤም 23 በመባል የሚታወቀው ታጣቂ ቡድን ጋኦማን ለመቆጣጠር የአካባቢው ሰዎች ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቀቂያ መስጠቱም ታውቋል ፡፡ ጋኦማ ለኮንጎ አማጽያን ጠቃሚና ስትራቴጂክ ቦታ ስለሆነች ከመንግስት የጸጥታ አካላት ጋር ብዙ ጊዜ የሚዋጉባት ግዛት እንደሆነች ይነገራል፡፡
የዓይን እማኞች እንደገለጹት በኤም 23 ታጣቂ ቡድንና እና በመንግስት የጸጥታ አካላት መካከል የነበረው ውጊያ ፤ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ነበር ፡፡ ዘገባው አፍሪካ ነውስ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook –https://www.facebook.com/ethiopiannbc












