አዲስ አበባ | ጥር 30፤ 2016| NBC ETHIOPIA -የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላድሜር ፑቲን ተቀናቃኝ ቦሪሰ ናዴዝዲን ከሩሲያ ምርጫ መታገዳቸው ተገለጸ ፡፡

የሩሲያ የምርጫ ኮሚሽን ጸረ- ጦርነት አቋም ያላቸውን ቦሪስን በሚቀጥለው ወር በሚካሄደው የሩሲያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዳይሳተፉ ከልክሏል ተብሏል፡፡
ቦሪስ ሩሲያ በዩክሬን የምታደርገውን ጦርነት ማቆም እንዳለባት ፑቲንን ብዙ ጊዜ በመተቸት ይታወቃሉ፡
በምርጫው እጩ ለመሆን የሚያስችላቸውን 15 በመቶ ፊርማ ማግኘታቸውን ለምርጫ ኮሚሽን ቢያቀርቡም ሀሳባውን ውድቅ አድርገውታል ፡፡
ቦሪስ በመላው ሩሲያ 200 ሺህ ፊርማ ስላገኘሁ ምንም የሚያቆመኝ የለም ጉዳዩንም ወደ ሩሲያ ፍርድ ቤት እወስደዋለሁ ቢሉም፤ የሩሲያ ምርጫ ኮሚሽን በበኩሉ ቦሪስ 9 ሺህ ፊርማ ብቻ ነው የሰበሰቡት በማለት ተቃውሟቸውን ውድቅ አድርጎታል ፡፡ ዘገባው የቢቢሲ ነው ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት