አዲስ አበባ | ጥር 24፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባላትና ሌሎች ክልላዊ ተቋማት በአፍጋኒስታን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ለመወያየት የፊታችን የካቲት 18-19 2024 በኳታር ዶሃ ለመገናኘት ቀጠሮ መያዛቸው ተገለጸ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የነፍስ አድን ቡድን አባላት እንዳስታወቁት ፤ አብዛኛው የአፍጋኒስታን ህዝብ ዓለምአቀፍ እርዳታ ፈላጊ ሆኗል ፡፡
ታሊባን የአፍጋኒስታንን በትረ ስልጣን በነሀሴ 2021 ከጨበጠ በኋላ የዜጎቹን ጥያቄ አልፈታም ፤ የጭቆና አስተዳደር መስርቷል እየተባለ ወቀሳ ይቀርብበታል ፡፡
ተሳታፊ ቡድኖች በአፍጋኒስታን ዕውቅና ያለው መንግስት መመስረት አለበት በማለት እስካሁን ድረስ እየታገሉ እንደሚገኙ ታውቋል ፡፡
በፈረንጆቹ ባለፈው ጥር 29 የቻይና፤ ሩሲያ፤ ኢራን፤ የህንድና ኢንዶኒዢያ ባለስልጣናት ቀጠናዊ ትበብርን ለማጎልበት በካቡል አፍጋኒስታን ተሰብስበው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ዘገባው የቲ አር ቲ ወርልድ ነው ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv