አዲስ አበባ | ጥር 22፤ 2016| NBC ETHIOPIA -የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በ2016 በጀት አመት ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በሀገሪቱ የኢንፎርሜሽን መሠረተ ልማት ላይ ሊደርሱ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን በመከላከልና የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በማረጋገጥ ረገድ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጿል።
በበጀት አመቱ 4623 የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸው የተገለፀ ሲሆን ከእዚህ ውስጥ 98.56% የሚሆኑትን ማክሸፍ ተችሏል ብሏል።
የተቃጣው ጥቃት ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ115% መጨመሩን የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ ገልፀዋል።
ባንኮችና የፋይናንስ ተቋማት፣ የፀጥታና ደህንነት ተቋማት፣ መገናኛ ብዙሃን ዋነኞቹ የጥቃቱ ኢላማ ነበሩ።
ሙከራዎቹ በሀገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችሉ ነበር የተባለ ሲሆን አስተዳደሩ ሙከራዎቹን ለማክሸፍ በሰራው ስራ ከ10.5 ቢሊዮን ብር በላይ ከኪሳራ ማዳን ተችሏል ብሏል።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












