አዲስ አበባ | ጥር 20፤ 2016| NBC ETHIOPIA-ሰሜን ኮርያ በቀናት ልዩነት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ምስራቅ ባህር ዳርቻ ሚሳኤል አስወንጭፋለች።

የባህር ሰርጓጅ መርከብ ላይ በኪም ጁንግ ኡን ትዕዛዝ የተፈጸመው ሙከራ ሀገሪቱ ዘመናዊ የክሩዝ ሚሳኤል ቲክኖሎጅዋን እያሳደገች ለመሆኑ አመላካች ነው ተብሏል፡፡ ፒንግያንንግ ባህር ላይ ያስወነጨፈችው ሚሳኤል ፑልሀዋሳል 3-31 እንደሚባል ታውቋል።
የደቡብ ኮርያ ወታደራዊ ባለስልጣናት ሰሜን ኮርያ ሲንፖ ወደብ ላይ ሚሳኤል ማስወንጨፏ ገልጸው ዝርዝር መረጃ ከመስጠት መቆጠባቸውን የዘገበው አልጀዚራ ነው ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv