አዲስ አበባ | ጥር 17፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መንግስት ወደ ሀይቲ የሚልካቸውን የፖሊስ መኮንን እንዳይሄዱ አገደ።
የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች እንደሚሉት የኬንያ መንግስት የሀገሪቱን ብሄራዊ ደህንነት አደጋ ላይ ስለሚጥል ይህን የማድረግና የፖሊስ መኮንኖችን ወደ ውጭ ሀገር የመላክ ስልጣን የለውም፡፡
ወደ ሀይቲ ሰላም ለማስከበር መሄድ ያለባቸው ፖሊስ ሞኮንንኖች ሳይሆኑ የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ነው በሚል ነው ፍርድ ቤቱ ድርጊቱን ያገደው።
ባለፈው ዓመት ኬንያ በፍቃደኝነት የሀይቲ ጋንግስተሮችን የሚዋጉ የጸጥታ አባላትን ልካ እንደነበር ታውቋል ፡፡ ከዚህ በፊት የሀይቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሪየል ሄንሪ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ሀይል እንዲገባ መጠየቃቸው ይታወሳል ፡፡
በሀይቲ ዋና ከተማ ፖርታኡ ፕሪንስ 80 በመቶ በጋንግስተሮች ቁጥጥር ስር እንደነበረች ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሪየል ሄንሪ መናገራቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv