አዲስ አበባ | ጥር 16፤ 2016| NBC ETHIOPIA-የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንና አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በትብብር በሀገራዊ ምክክር ላይ የሚያተኩር መድረክ አዘጋጅተዋል።


“ለሀገራዊ ምክክርና መግባባት የምሁራን አበርክቶ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው መድረኩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት በሚኖራቸው ሚና ላይ ምክክር እየተደረገ ነው።
በመድረኩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን በምክክሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል። በተጨማሪም ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ ያለው ልምድ፤ ተስፋና ስጋቶች ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን አለም አቀፋዊ ልምዶችም ተዳስሰውበታል።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












