አዲስ አበባ | ጥር 13፤ 2016| NBC ETHIOPIA -በአዲስ አበባ 8ተኛው ከተማ አቀፍ ፌስቲቫል እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሀላፊ አስፋው ኩማ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ፌስቲቫሉ ከጥር 16 ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት በአዲስ አበባ ሙዚየም እንደሚካሄድ ገልፀዋል።
ፌስቲቫሉ <<አንባቢ ትውልድ ለሀገር ብልፅግና>> በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል። በከተማው ያለውን የንባብ ባህል ከማሳደግ ባለፈ የፌስቲቫሉ መካሄዱ የቤተ-መጻሕፍትን አሰራርን ለማዘመን፣ በዘርፉ የሚስተዋለው ችግር ለመለየት እና ለመቅረፍ ይረዳል ተብሏል።
በእለቱ ደራሲያን፣ መፅሐፍ ሻጮች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የግል እና የመንግስት ቤተ መፅሐፍቶች እንደሚሳተፉበት ተገልጿል። 50 የሚደርሱ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች በፌስቲቫሉ ይሳተፋሉ።
በሀሴት ሀይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












