አዲስ አበባ | ጥር 09፤ 2016| NBC ETHIOPIA – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም በሳምንቱ ከውጭ ግንኙነት ጋር በተያያዘ ያሉ ጉዳዮችን አስመልክቶ ማብራርያ ሰጥተዋል::

አምባሳደሩ በመግለጫቸው የአረብ ሊግ ከሰሞኑ በኢትዮጵያና በሶማሌ ላንድ መካከል የተፈረመው ስምምነት አለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው ሲል ያወጣው መግለጫ ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቀዋል::
ቃል አቀባዩ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚህ ሹክሪ ኢትዮጵያ በቀጠናው ለሚፈጠሩ ግጭቶች መንስኤ ናት ሲሉ የሰጡትም አስተያየት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የሚመጥን አለመሆኑንም አመላክተዋል::

ኢትዮጵያ ከኬንያም ሆነ ከሶማሊያ ጋር ያላት የንግድም እንዲሁም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አሁንም እንደ ቀድሞ መቀጠሉን አምባሳደር መለስ አለም አስታውቀዋል::
በአክረም ኑርያ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












