አዲስ አበባ | ጥር 03፤ 2016| NBC ETHIOPIA – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2015 የግብር ዘመን ግብር በወቅቱ እና በአግባቡ ለከፈሉ የከተማዋ ታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ።
ለከተማዋ ሁለንተናዊ ዕድገት ግብር በወቅቱና በአግባቡ በመክፈል የዜግነት ግዴታቸውን እየተወጡ ያሉ የከተማዋ ግብር ከፋዮች በ2015 የግብር ዘመን ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ የእውቅናና ሽልማት እንደሚያበረከትላቸው ተገልጿል።
የገቢ አሰባሰቡን ለማሳደግ “ግብር ለሀገር ክብር”በሚል መሪ ሀሳብ ከ 562 በላይ ታማኝ ግብር ከፋዮች የሚያሳትፈው የእውቅናና የሽልማት መርሀ ግብር የፊታችን ጥር 5 እንደሚያካሂድ ቢሮው በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።
በሀይማኖት ወርቁ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram- https://t.me/nbcethiopiatv












