አዲስ አበባ | ታህሳስ 26፤ 2016| NBC ETHIOPIA -የማንቺስተር ዩናይትዱ ግብ ጠባቂ በአፍሪካ ዋንጫው ምክንያት ሀገሩ ካሜሮንን የሚቀላቀልበት ጊዜ እስካሁን እርግጥ አለመሆኑ ተነግሯል ቀያይ ሰይጣኖቹ በአህጉራዊ መድረክ ዋንጫ ምክንያት ጥቂት ጨዋታዎችን ያለ ኦናና ለመጫወት የሚገደዱ ይሆናል።

ኦናና በፈረንጆቹ ጥር 14 ዩናይትድ በሜዳው ኦልድትራፎርድ ቶትንሀም ሆትስፐር በፕሪሚየር ሊጉ በሚያስተናግድበት ጨዋታ ላይ ተጫውቶ የሪጎበርት ሶንግ ቡድንን እንደሚቀላቀል በመግለጽ ላይ ነው።
ካሜሮን በበኩሏ የመጀመሪያ የአህጉራዊ መድረክ የምድብ ጨዋታዋን በሀያ አራት ሰዓት ልዩነት ከጊኒ ጋር ታደርጋለች።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv











