የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአቅመ ደካማ ወገኖች 389 የመኖሪያ ቤቶችን አበረከተ። የተለያዩ ባለሀብቶችና በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር የተገነቡት ቤቶች 76 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው ናቸው ተብሏል።


ከቤቶች ስጦታ በተጨማሪ ከተማ አስተዳደሩ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት አከናውኗል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ ልበ ቀና ባለሃብቶችንና ሌሎች አቅሞቻችንን በማስተባበር በከተማችን 389 ቤቶችን ገንብተን በማጠናቀቅ ለአቅመ ደካሞችና ለሃገር ባለውለታ ነዋሪዎቻችን በማስረከብ ችግሮቻቸውን አቃለናል ሲሊ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።


በልብ ቀናነት ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት ለሌሎች ደስታን የምትለግሱ ሁሉ፣ በጎነት አያጎድልምና በተጠቃሚዎቹ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁም ነው ያሉት፡፡
በሰላማዊት ወንድወሰን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram- https://t.me/nbcethiopiatv