Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

የሰቆጣ ቃል ኪዳን የአፈፃፀም ግምገማ እና የዕቅድ ማፅደቂያ ውይይት እየተካሄደ ነው

January 1, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አዲስ አበባ | ታህሳስ 22 ፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የሰቆጣ ቃል ኪዳን የ2015 ዓ.ም አፈፃፀም ግምገማ፤ የ2016 ዓ.ም እቅድ ማጸደቂያ፤ የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ማስተዋወቂያ መድረክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የየክልሉ የግብርና ሚኒስትሮች እና የፌዴራል ሚኒስትሮች በተገኙበት በመካሄድ ላይ ነው።

በመድረኩ ቅንጅታዊ አሰራር ተዘርግቶ ወደ ስራ ከተገባ በኋላ፥ ጤና ሚኒስቴር እና የግብርና ሚኒስቴር ከምግብና ስርዓተ ምግብ ተባባሪ ሴክተር መስሪያቤቶች እና አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በርካታ ተግባራት መከናወናቸው ተብራርቷል።

በውይይቱ በ40 ወረዳዎች የነበረውን የሰቆጣ ቃል ኪዳን የሙከራ ምዕራፍ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ወደ 240 ወረዳዎች በማስፋት እየተገበረ መሆኑ ተገልጿል።

ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት እና IFPRI ጋር በተካሄደው የተጽዕኖ ግምገማ ጥናት በ2014 ዓ.ም ብቻ 59ሺ 717 ህጻናትን ከመቀጨር ፣ 2ሺ 904 ልጆችን ከሞት መታደግ እንደተቻለ ተብራርቷል፡፡

በኢትዩጵያ የሚታየው የመቀንጨር ችግር ከግዜ ወደ ግዜ መሻሻሎች ቢያሳይም ፥ 39 በመቶ የመቀንጨር፣ 11 በመቶ የመቀጨጭ ችግር እድሜያቸው ከ አምስት አመት በታች በሆኑ ህጻናት ላይ እንደተከሰተ ተመላክቷል።

በቀጣይ ከ2016 እስከ 2018 ዓ.ም ይህን ፕሮግራም በ700 ወረዳዎች በማስፋት ከ5 ሚሊዮን በላይ ህፃናትን ከመቀንጨር ለመታደግ የሁሉም ርብርብ ይሻል ተብሏል።

የትግበራ ዕቅዱን በስራ ላይ ለማዋል ክልሎች፣ ከተማ መስተዳደሮች እና አጋር አካላት የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

የ2015 ዓ.ም የሰቆጣ ቃል ኪዳን እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2016 ዓ.ም እቅድና በጀት ማፀደቅ፤ የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ማስተዋወቅ ፍኖተ ካርታና ሀገራዊ ዳሰሳን ማስተዋወቅ፤ የምግብ ስርዓትን እና ስርዓተ ምግብ ትግበራን ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጠናከር ምክር ቤት ለማቋቋም እና በክልሎች ደረጃ የተከናወኑትን እና የአመራሩን ክትትል የሚሹ ጉዳዮች ላይ በውይይቱ ትኩረት የተደረገባቸው ጉዳዮች ናቸው።

ዕድሜያቸው ከሁለት ዓመት በታች በሆኑ ህጻናት ላይ የሚከሰተውን የመቀንጨር ችግር በ2022 ዓ.ም ዜሮ ለማድረግ በ2007 ዓ.ም የሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮግራም ይፋ መደረጉ ይታወሳል።

ቃልኪዳኑ በሰቆጣ ከተማ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዲሁም የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና የከተማ ከንቲባዎች በተገኙበት በነሐሴ 2007 ዓ.ም በሰቆጣ ከተማ ነበር የተፈረመው።

በወቅቱ ከ7.8 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሕጻናትን በ15 ዓመት ከመቀንጨር ለመታደግ ሀገራዊ ቃልኪዳን ተገብቷል፡፡

በሰላማዊት ወንድወሰን

YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA

TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia

Website – https://nbcethiopia.com/news/

Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/

#NBC_ETHIOPIA

#ሆኖ_መገኘት

ShareTweetShare
Previous Post

በፈረንጆቹ 2023 ህይወታቸውን ያጡ ታዋቂ የፊልም ተዋንያን

Next Post

የጃፓን የመሬት መንቀጥቀጥ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
7
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
7
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
14
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
50
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
37
Next Post
የጃፓን የመሬት መንቀጥቀጥ

የጃፓን የመሬት መንቀጥቀጥ

በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የስኳር በሽታ (GESTATIONAL DM)

በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የስኳር በሽታ (GESTATIONAL DM)

”ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቃሚ እንድትሆን የተፈረመው ስምምነት ለዘመናት የተቆለፈውን በር የሚከፍት ነው”

''ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቃሚ እንድትሆን የተፈረመው ስምምነት ለዘመናት የተቆለፈውን በር የሚከፍት ነው''

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?