አዲስ አበባ | ታህሳስ 18፤ 2016| NBC ETHIOPIA- ፖርቱጋላዊው የማንችስተር ሲቲ አማካይ በርናርዶ ሲልቫ በፕሪሚየር ሊጉ 37 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ለጓደኞቹ በማመቻቸት የአገሩ ልጅ ክርስትያኖ ሮናልዶን ክብረ ወሰን ተጋርቷል።
የ29 አመቱ ሲልቫ ትላንት ምሽት ጉዲሰን ፓርክ ላይ ኤቨርተንን 3-1 በሆነ ዉጤት ሲያሸንፉ የአንድ ጎልና አሲስት አበርክቶት ነበረው።
ፊል ፎደን ከመመራት ወደ አቻነት የመለሰቻቸውን ጎል በ53ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው በርናርዶ ሲልቫ ከሳጥን ዉጭ ያሻገረለትን ኳስ ነበር።
የጨዋታዉን ማሳረጊያ ጎል በ86ኛው ደቂቃ ያስቆጠረውም ይህ ፖርቱጋላዊ ኢንተርናሽናል ነበር።
ሲልቫ በክረምት የዝውውር መስኮት ባርሴሎናና ፓሪሴን ዠርመንን ጨምሮ የበርካታ የሳውዲና የአውሮፓ ክለቦች የዝውውር ራዳር ውስጥ ገብቶ ነበር።
ይሁንና በኋላ ላይ በዉሃ ሰማያዊዎቹ ቤት እስከ 2026 ድረስ የሚያቆየውን ዉል ማራዘሙ ይታወሳል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












