አዲስ አበባ | ታህሳስ 11 ፤ 2016 – በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሚመራው የልዑካን ቡድን በቼንዱ እያደረገ ባለው የስራ ጉብኝት ላይ የባህርዳር እና ዱጃንየ ከተሞች ዛሬ የእህትማማችነት ስምምነት ተፈራርመዋል::


የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ጎሹ እንዳለማው እና የዱጃንየ ከተማ ከንቲባ ጃንያ ዳን ስምምነቱን የተፈራረሙ ሲሆን በቀጣይ ሁለቱ ከተሞች በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝም፣ በፓርክ ልማትና አስተዳደር እንዲሁም በአረንጏዴ ልማት ስራዎች ዙሪያ አብሮ ለመስራት ተስማምተዋል::
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv