አዲስ አበባ | ታህሳስ 10፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የኮሎራዶ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዶናልድ ትራምፕ በግዛቱ ውስጥ በሚቀጥለው ዓመት ለፕሬዝዳንትነት መወዳደር እንደማይችሉ አስታውቋል፡፡

ትራምፕ ከሦስት ዓመታት በፊት በአሜሪካ ካፒቶል ግርግር ላይ አመጽ በመፈጸማቸው ምክንያት ለምርጫ እጩነት ብቁ አይደሉም ሲል ፍርድ ቤቱ የዳኝነት ብይን ሰጥቷል ፡፡ ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው ምርጫ አሁንም ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት መወዳደር ቢችሉም ነገር የአሁኑ ክስ ነገሮችን የበለጠ አስቸጋሪ ሊያደርግባቸው ይችላል ተብሏል ።
የትራምፕ የምርጫ አስፈጻሚዎች ጉዳዩን ለአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ለማቅረብ እንደሚፈልጉ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል ።
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












