አዲስ አበባ | ታህሳስ 01፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ጊታሪስት እንዲሁም በዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያኖረው ኤልያስ መልካ ታህሳስ 01/1970 በዛሬው እለት ከአባቱ ከአቶ መልካ ገረሱ እና ከእናቱ ወ/ሮ አፀደ ፈለቀ በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ሰባተኛ በሚባል ሰፈር ነበር የተወለደው፡፡

ከያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ቼሎ የሙዚቃ መሳሪያን ተምሮ ከጨረሰ በኋላ ከመምህሩ አክሊሉ ዘውዴ፣ ከእዝራ አባተ፤ ከያሬድ ተፈራና ከሌሎችም ጋር በመሆን በመዲና ባንድ ውስጥ፤ ከዜማ ላስታስና አፍሮ ሳውንድስ ባንዶች ጋር ሰርቷል። ኤልያስ ከ40 በላይ የስቱዲዮ አልበሞችን እና በርካታ ነጠላ ዜማዎችን አዘጋጅቷል።
ኤልያስ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከብዙ ሰዎች ጋር በመሆን ጣዕም ያላቸውን ሙዚቃዎች ሰርቷል፡፡ ከአርቲስት መሃሙድ አህመድ ፣ቴዲ አፍሮ፣ ጎሳዬ ተስፋዬ፣ ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ ፣ ሚካያ በሀይሉ፣ እዮብ መኮንን፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ትዕግስት በቀለ፣ ሀይሌ ሩትስ ፣ ጌጤ አንለይ ፣ ልኡል ሀይሉ ቤሪ፣ ዳን አድማሱ ከሰራላቸው አርቲስቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
እንደ ኤች አይ ቪ ኤድስ እና የትራፊክ አደጋ ባሉ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ሙዚቃን ፅፎም አዘጋጅቷል።
ኤልያስ መልካ በኩላሊት እና በስኳር ህመም ሲታገል ቆይቶ መስከረም 24 2012 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶል።
ምንም እንኳን በ41 አመቱ ህይወቱ ቢያልፍም ኤልያስ ብዙዎች ሊያልሙት ከሚችሉት በላይ ያስመዘገበ ሲሆን ስሙም በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራን መያዙ ይታወቃል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












