አዲስ አበባ | ህዳር 26፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የኢንሹራንስ ዘርፍን የሚደግፍ ቢማላብ ኢትዮጵያ የተሰኘ ፕሮግራም በይፋ ስራ ጀመረ::

በመጀመሪያ በፋይናንሻል ሴክተር ዲፕኒንግ ኤፍ. ኤስ. ዲ አፍሪካ በአህጉር ደረጃ ተተግብሮ በኤፍ. ኤስ. ዲ ኢትዮጵያ ወደ ስራ የገባው በቢል ኤንድ ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን አጋሮች የተደገፈው ይህ ፕሮግራም በኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ዘርፍ ላይ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ አካታች መፍትሄዎችን እና ፈጠራዎችን በማጎልበት የአገሪቷ ኢኮኖሚ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ነው ተብሏል።
ወደ ትግበራ የገባው ቢማላብ ኢትዮጵያ የፈጠራ ባለቤቶች የሆኑ መፍትሄ ፈጣሪዎች የሚገጥሟቸውን የፋይናንስ እና የሰለጠኑ ባለሙያዎች እጥረት ያሉ መሰል ችግሮችን የሚፈቱበትን መንገድ ለማሳየት ያለመ ፕሮግራም መሆኑ ነው የተነገረው።
ሰብለ ወንድማገኝ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












